Entries by tc

በትሮንዳሔም የ ፩ ቀን ጉባኤ ተካሄደ

ለመንፈሳዊ አገልግሎት ከኢትዮጵያ ተጋብዘው ኖርዌይ በመጡት በዘማሪ ዲያቆን እንግዳወርቅ በቀለ እሁድ ህዳር ፳፰ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም በትሮንዳሔምና አካባቢው ለሚገኙ ምእመናን ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መዝሙርና ስብከተ ወንጌልን ያካተተ ጉባኤ አካሄደ። ጉባኤውን በፎቶ ይመልከቱ

የ፫ ቀናት መንፈሳዊ ጉባኤ ተካሄደ

በቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በትሮንዳሔ በአካባቢው ለሚገኙ ምእመናን ለሦስት ተከታታይ ቀናት ከጥቅምት ፳፰ እስከ ፴ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም መንፈሳዊ ጉባኤ ተካሄደ። በጉባኤውም ላይ ቀሲስ ወንድወሰን ሶርሳን በመጋበዝ እምነት እና በዓለ መድኃኒዓለምን በተመለከተ ሰፋ ባለ መልኩ ትምህርተ ወንጌል ተሰጧል። ከምእመናን በቀረቡ ጥያቄዎች ላይ ማብራሪያ ከተሰጠ በኋላ መርሃ ግብሩ በሥርዓተ ጸሎት ተጠናቋል። ጉባኤውን በፎቶ ይመልከቱ

የ፳፻፯ ዓ.ም የመስቀል በዓል ተከበረ

በቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትሮንዳሄም የመስቀል በዓል ዓርብ መስከረም ፲፮ ፳፻፯ ዓ.ም በስርዓተ ጸሎት፣ ደመራ በማብራት እና በያሬዳዊ ዝማሬ በየአመቱ እንደሚደረገው በመሆልት የተማሪዎች መኪና ማቆሚያ ቦታ ላይ ቀሲስ ተስፋዬ ፣ የደብሩ መዘምራንና በአካባቢው የሚኖሩ ምእመናንና ምእመናት በተገኙበት በዓሉ በድምቀት ተከበረ። ቀሲስ ተስፋዬ በዓሉን የሚመለከት ትምህርተ ወንጌል አስተላልፈዋል እንዲሁም የደብሩ መዘምራን የመዝሙር አገልግሎት […]

የደብረ ታቦር በዓል እና ጾመ ፍልሰታን ምክንያት በማድረግ ጉባኤ ተካሄደ

በቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትሮንዳሄም የደብረ ታቦር በዓልና ጾመ ፍልሰታን ምክንያት በማድረግ ለ፪ ቀናት ማለትም ነሐሴ ፳፫ እና ፳፬ ፳፻፮ ዓ.ም የአካባቢው ምእመናንና ምእመናት በተገኙበት መንፈሳዊ ጉባኤ ተካሄደ። በጉባኤውም ላይ መላከ ጽዮን ቆሞስ አባ ሙሴ በመገኘት የስብከተ ወንጌል አገልግሎትና ስርዓተ ቅዳሴ እንዲከናወን በማድረግ በዓሉ በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል። ጉባኤውን በፎቶ ይመልከቱ

የ፫ ቀናት መንፈሳዊ ጉባኤ ተካሄደ

በቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትሮንዳሄም በመምህር ምሥጢረ ሥላሴ ማናዬ ከነሐሴ ፪ እስከ ፬ ፳፻፮ ዓ.ም መንፈሳዊ ጉባኤ ተካሄደ። በጉባኤውም ላይ በአካባቢው ለሚኖሩ ምእመናንና ምእመናት የሦስት ቀን የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ተካፋይ እንዲሆኑ ተደርጓል። ጉባኤውም በስርዓተ ጸሎት ተጀምሮ በእግዚአብሔር መልካም ፍቃድ በጸሎት ተጠናቋል። ጉባኤውን በፎቶ ይመልከቱ

የ፳፻፮ ዓ.ም. የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ ክብረ በዓል በደመቀ መልኩ ተከበረ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የትሮንዳሔም ቅዱስ ጊዮርጊስ ደብር የ፳፻፮ ዓ.ም. የዳግም ትንሣኤንና የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ ክብረ በዓላት ከተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት ተጋብዘው በመጡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ የሰንበት ት/ቤት መዘምራን፣ ምእመናን እና ምእመናት በተገኙበት ዓርብ ሚያዚያ ፲፯ እና ቅዳሜ ሚያዚያ ፲፰ በታላቅ ድምቀት አከበረ። በዓሉ በማሕሌት፣ በቅዳሴ፣ በትምህርተ ወንጌልና በመዝሙር የተከበረ ሲሆን ያሬዳዊ ዝማሬም በደብሩ መዘምራን ቀርቧል። በተጨማሪም የላቫንጋርና […]

የ፳፻፮ ዓ.ም. የስቅለትና የትንሣኤ በዓላት አከባበር

የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ስቅለትና በዓለ ትንሣኤ በቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትሮንዳሔም አጥቢያ በሚገኙ ምእመናን እና ምእመናት በዕለቱ ተከብሮ ዋለ። የበዓሉን አከባበር በፎቶ ይመልከቱ

የ፳፻፮ ዓ.ም. ደብረዘይት በዓል በደመቀ መልኩ ተከበረ

ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትሮንዳሔም የደብረዘይት በዓልን ከመጋቢት ፲፪ እስከ ፲፫፣ ፳፻፮ ዓ.ም. ከተለያዩ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት ከመጡ አባቶች ካህናት እና ወንድሞች ዲያቆናት እንዲሁም በአካባቢው ከሚኖሩ ምእመናንና ምእመናትጋር በቅዳሴ፣ በስብከተ ወንጌልና በያሬዳዊ ዝማሬ በታላቅ ድምቀት አከበረ። የበዓሉን አከባበር በፎቶ ይመልከቱ

የትሮንዳሔም ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላላ ጉባኤውን አደረገ

ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትሮንዳሔም እሁድ ጥር ፲፰ ቀን ፳፻፮ ዓ. ም ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ። ጉባኤው በጸሎት ከተጀመረ በኋላ እ.ኤ.አ የ2013 እቅድ አፈጻጸምና የኦዲት ሪፖርት እንዲሁም የ2014/እ.ኤ.አ/ ዕቅድ ቀርቦ ሰፋ ያለ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ጸድቋል። ጉባኤው የተጀመረውን ዓመት በኃላፊነት ሊያገለግሉ የሚችሉ ሰባት መንፈሳዊ የሰበካ ጉባኤ አባላትን መርጦ ከአጸደቀ በኋላ በጸሎት ተዘግቷል። ጠቅላላ […]

የጥምቀት በዓል በኖርዌይ በድምቀት ተከበረ

በኖርዌይ በተለያዩ ከተማ የሚገኙት ስድስት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናት ማለትም የኦስሎ ቅዱስ ገብርኤል፤ የስታቫንጋር መድኃኔዓለም፤ የክርስቲያንሳንድ ቅድስት ድንግል ማርያም፤ የበርገን እመቤታችንና ቅዱስ ሚካኤል እና የትሮንዳሔም ቅዱስ ጊዮርጊስ ታቦታት አንድ ላይ በመሆን የጌታችን የአምላካችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን በዓለ ጥምቀት በበርገንበታላቅ ድምቀት አከበሩ። በዓሉ በኖርዌይና ከተለያዩ ሃገራት በመጡ አባቶች ካህናትና ምእመናን በተገኙበት በቤተ ክርስቲያናችን ስርዓት መሰረት […]