Entries by tc

የሊቀ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ ክብረ በዓል ሚያዚያ ፳ እና ፳፩ ፥ ፳፻፱ ዓ.ም በድምቀት ተከበረ

በቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትሮንዳሔም የሚያዝያ ፳፫፥፳፻፱ ዓ.ም የሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ ክብረ በዓል በተለያዩ አውሮፓ ሀገራት ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ተጋብዘው በመጡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ ከመላው ኖርዌይ እንዲሁም ከትሮንዳሔምና አካባቢው በተገኙ የሰንበት ት/ቤት መዘምራን፣ ምእመናንና ምእመናት ዓርብ ሚያዚያ ፳ እና ቅዳሜ ሚያዚያ ፳፩ ፥፳፻፱ ዓ.ም በታላቅ ድምቀት ተከበረ። በዓሉ ዓርብ እለት ምሽት […]

የ፳፻፱ የጌታችን ስቅለት እና ትንሣኤ በዓላት በቤተክርስቲያናችን በደማቁ ተከበረ

ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ሞተ ወኬዶ ለሞት ለእለ ውስተ መቃብር ወሃበ ሕይወተ ዘለዓለመ ዕረፍተ። የ፳፻፱ ዓ.ም የጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት እና ትንሣኤ በዓላት በቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በትሮንዳሔም በድምቀት ተከበረ። በዓላቱ ከስዊድን ተጋብዘው በመጡት አባታችን መልአከ ህይወት ፍስሐ አባ ገብረማርያም ቢምረው እና በርካታ ቁጥር ባለው የትሮንዳሄምና አካባቢው ምእመን ሱታፌ በተለያዩ አገልግሎቶች […]

የደብረ ዘይት በዓል በድምቀት ተከበረ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/ በሰሜን ምዕራብ አውሮጳ ሀገረ ስብከት የትሮንዳሔም ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በትሮንዳሔም የደብረ ዘይት በዓል መጋቢት 9፥ 2009 ዓ.ም ከስዊድን በመጡት አባት አባ ገብረ ጊዮርጊስ እና በትሮንዳሄምና አካባቢው በሚገኙ ምእመናን በቅዳሴ፣ በስብከተ ወንጌልና በንሰሃ ዝማሬዎች በድምቀት ተከበረ። በበዓሉም ላይ በአባ ጊዮርጊስ ዕለቱን የተመለከተ ትምህርተ ወንጌል ተሰጥቷል። የበዓሉን አከባበር በፎት ይመልከቱ!

የጥምቀት በዓል ለመጀመሪያ ጊዜ በትሮንዳሔም በድምቀት ተከበረ

ጥር ፯ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት በትሮንዳሔም ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አዘጋጅነት በተካሄደው የጥምቀት በዓል ላይ ከበርገን የመንበረ ልዑል ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን፣ ከስታቫንገር የመድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን፣ ከክርስቲያንሳንድ የቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን፣ በተጨማሪም ከትሮንዳሔም ቅዱስ ሚካኤል የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አገልጋይ ካህናት፣ ዲያቆናት፣ የሰንበት ትምህርት ቤት […]

ለ፪ ቀናት የቆየ ልዩ መንፈሳዊ ጉባዔ ተካሄደ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሰሜን ምዕራብ አውሮጳ ሃገረ ስብከት የትሮንዳሔም ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ለአገልግሎት ከኢትዮጵያ ወደ አውሮጳ በመጡት በኩረ መዘምራን ኪነጥበብ ወ/ቂርቆስ እና መጋቤ ሐዲስ ምሥጢረ ሥላሴ ማናዬ ለ፪ ቀናት የቆየ የዝማሬና የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ተካሄደ። ጉባዔው ከትሮንዳሔምና አካባቢው በተገኙ ምዕመናን ቅዳሜ መስከረም ፳፰ በ 9:00 ሰዓት እንዲሁም መስከረም ፳፱ በ 10:30 ሰዓት ስለሃገራችን ሰላምና መረጋጋት የዘወትርና […]

የ ፳፻፱ ዓ.ም መስቀል ደመራ በዓል በድምቀት ተከበረ፤ የ፫ ቀናት መንፈሳዊ ጉባዔም ተካሄደ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሰሜን ምዕራብ አውሮጳ ሃገረ ስብከት የትሮንዳሔም ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ለአገልግሎት ከኢትዮጵያ ወደ አውሮጳ በመጡትና ወደ አጥቢያችን የመስቀልን በዓል ለማክበር በተጋበዙት መምህር ፍቃዱ ሳህሌ የ፫ ቀናት ጉባዔ ተካሄደ። ቅዳሜ፣ እሁድ እንዲሁም ማክሰኞ (ከመስከረም ፲፬ – ፲፯) በተካሄደው ጉባዔ ላይ በተለያዩ ርዕሶች መንፈሳዊ ትምህርት ለትሮንዳሔምና አካባቢው ምዕመናን የተሰጠ ሲሆን ከምዕመናን በተነሱ ጥያቄዎች ላይ ምላሽና ምክረ […]

የ፳፻፰ ዓ.ም የፍልሰታ ለማርያም ጾም አጋማሽ ቅዳሴና የአንድ ቀን ጉባኤ ተካሄደ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/በሰሜን ምዕራብ አውሮጳ ሀ/ስብከት የትሮንዳሔም ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ቅዳሜ ነሐሴ ፯፥፳፻፰ ዓ.ም ከኢትዮጵያ በመጡት ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ (ሊቀ መዘምር) የፍልሰታን ጾም በማስመልከት የቅዳሴ መርሐ ግብር የተከናወነ ሲሆን ከቅዳሴው በኋላ በአጥቢያው ሕጻናት አጫጭር መዝሙራት ቀርበዋል። ። በመቀጠልም በቀሲስ ምንዳዬ ዝማሬዎችና ዕለቱን የተመለከተ የወንጌል ትምህርት ተሰጥቷል። በመጨረሻም የዕለቱ መርሐ ግብር በአባታችን ቡራኬ ተፈጽሟል። በነጋታው እሁድ ነሐሴ ፰፥ […]

ልዩ መንፈሳዊ የሕፃናት ቀን በአጥቢያችን በታላቅ ድምቀት ተከበረ

በአይነቱ ልዩ የሆነና ሕጻናትን ያማከለ መርሐ ግብር በአጥቢያችን የቅዱስ ጊዮርጊስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በትሮንዳሄም ሰኔ ፲፪፥ ፳፻፰ ዓ.ም (June 19, 2016) ተካሄደ። የዕለቱ ዝግጅት በጸሎት ከተጀመረ በኋላ ሕፃን ሕርያቆስ እና ሕፃን ሊድያ በጋራ በመሆን በጣፋጭ የሕፃን አንደበታቸው አባታችን ሆይ በማድረስ የሕጻናቱ መርሐ ግብር በይፋ የተጀመረ ሲሆን የምሥጢራት ሁሉ መጀመርያ የሆነው ምሥጢረ ሥላሴን ሕፃን ሔርሜላ፣ ሕፃን ማሪያና፣ ሕፃን […]

የ፳፻፰ ዓ.ም ጰራቅሊጦስ በዓል በድምቀት ተከበረ

በቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትሮንዳሔም የ፳፻፰ ዓ.ም ጰራቅሊጦስ በዓል ሰኔ ፲፩፥፳፻፰ ዓ.ም (June 18, 2016) በቅዳሴ፣ በያሬዳዊ ዝማሬዎችና በስብከት ተከበረ። በዕለቱ ከዴንማርክ የተጋብዙት አባ ዘሚካኤል ዴሬሳ ፣ ከቅዱስ ሚካኤል የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዲያቆናት እንዲሁም በትሮንዳሄምና አካባቢው የሚኖሩ ምእመናን የተገኙ ሲሆን መርሐ ግብሩ ከንጋቱ 12:30 (06:30AM) ሰዓት በጸሎትና በምንባባት ከተጀመረ በኋላ በቅዳሴ […]