ኅዳር 7 ቀን በቅዱስ ጊዮርጊስ ሀገር በልዳ በስሙ ለመጀመሪያ ጊዜ ቤተክርስቲያን የታነፀበት ዕለት ነው። ይህ ታላቅ በዓል በትሮንድሃይም ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በማኅሌት፣ በቅዳሴ እና ፣ በዝማሬ በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል። በበዓሉ አረጋዊው አባት መልአከ ሕይወት ቀሲስ ጌጡ የኋላሸት ፣ ትሁትና ትጉህ የሆኑት መሪጌታ ሰሎሞን እንዲሁም ካህናትና ዲያቆናት ተገኝተዋል።