• ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ!

  • "ድምፁ መልካም በሆነ ጸናጽል አመስግኑት፤ እልልታ ባለው ጸናጽል አመስግኑት" መዝ 150፥5

ዜናዎች እና ወቅታዊ ክንውኖች

የትሮንዳሔም ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላላ ጉባኤውን አደረገ

ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትሮንዳሔም እሁድ ጥር ፲፰ ቀን ፳፻፮ ዓ. ም ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ። ጉባኤው በጸሎት ከተጀመረ በኋላ እ.ኤ.አ የ2013 እቅድ አፈጻጸምና የኦዲት ሪፖርት እንዲሁም የ2014/እ.ኤ.አ/ ዕቅድ ቀርቦ ሰፋ ያለ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ጸድቋል። ጉባኤው የተጀመረውን ዓመት በኃላፊነት ሊያገለግሉ የሚችሉ ሰባት መንፈሳዊ የሰበካ ጉባኤ አባላትን መርጦ ከአጸደቀ በኋላ በጸሎት ተዘግቷል። ጠቅላላ […]

የጥምቀት በዓል በኖርዌይ በድምቀት ተከበረ

በኖርዌይ በተለያዩ ከተማ የሚገኙት ስድስት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናት ማለትም የኦስሎ ቅዱስ ገብርኤል፤ የስታቫንጋር መድኃኔዓለም፤ የክርስቲያንሳንድ ቅድስት ድንግል ማርያም፤ የበርገን እመቤታችንና ቅዱስ ሚካኤል እና የትሮንዳሔም ቅዱስ ጊዮርጊስ ታቦታት አንድ ላይ በመሆን የጌታችን የአምላካችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን በዓለ ጥምቀት በበርገንበታላቅ ድምቀት አከበሩ። በዓሉ በኖርዌይና ከተለያዩ ሃገራት በመጡ አባቶች ካህናትና ምእመናን በተገኙበት በቤተ ክርስቲያናችን ስርዓት መሰረት […]

በትሮንዳሔም የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ተቋቋመ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የትሮንዳሔም ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰንበት ት/ቤት ከ 17 ዓመታት ጉዞ በኋላ ወደ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አደገ። ሰንበት ትምህርት ቤቱ እ.ኤ.አ በ 1995 «በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የትሮንዳሔም ሰንበት ት/ቤት» ተብሎ የተመሰረተ ሲሆን አሁን ቅዱስ እግዚአብሔር ፈቅዶ ታቦተ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ በሊቃነ ጳጳሳት ተባርኮ በመጋቢ ምስጢር ቆሞስ አባ ቴዎድሮስ አማካኝነት ወደ […]

ሰባቱ ምስጢራተ-ቤተክርስቲያን ለሦስት ተከታታይ ሳምንታት በትሮንዳሔም ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰ/ት/ቤት ተሰጠ

በኖርዎዌይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የትሮንዳሔም ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰንበት ትምህርት ቤት ለሦስት ተከታታይ ሳምንታት ማለትም ጥቅምት ፲፯ እና ፳፬ እንዲሁም ህዳር ፩ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ስለ ሰባቱ ምስጢራተ-ቤተክርስቲያን ተከታታይ ትምህርት ለአባላት በዕለተ ሰንበት ከጸሎት በኋላ ተሰጥቷል። ተከታታይ ትምህርቱ የተዘጋጀው የሰንበት ትምህርት ቤቱ አባላት ስለ ቅዱስ ቁርባንና ቅዱስ ጋብቻ ትምህርት እንዲሰጣቸዉ በጠየቁት መሰረት ነው። ትምህርቱን የሰጠዉ […]

የመስቀል በዓል አከባበር

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ! በትሮንዳሔም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ የቅዱስ ጊዮርጊስ ሰ/ት/ቤት የደመራ በዓልን ሐሙስ መስከረም ፲፮ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ደመራ በማብራት እና በዝማሬ በድምቀት አከበረ። የመስቀልን በዓል ምክንያት በማድረግም በዓመታዊው መርሃ ግብራችን መሰረት ቅዳሜ መስከረም ፲፰ ቀን ፳፻፮ዓ.ም. በአካባቢው የሚኖሩ ምእመናንና ምዕመናት በተገኙበት የቅዳሴ መርሃ ግብር ተደርጓል። ዘመነ ማርቆስ የሰላም፣ የፍቅር፣ የጤና፣ የንስሐና […]

በፌስቡክ ያግኙን

የአስተዳዳሪው መልእክት

ያለ ሥርዓት አልሄድንም  (2ኛ ተሰ 3÷7)

ማንኛውም ፍጡር በተፈጥሮ የተሰጠው ሕግና ሥርዓት አለው ይልቁንም ሰው የተፈጠረውና የሚኖረው ሲመራም የኖረበት ሥርዓት አለው። አፈጻጸማቸውና አጠቃቀማቸው ስለ ሥርዓትም ያላቸው ግንዛቤና የሚሰጡት ዋጋ የተለያየ ይሁን እንጅ በዓለም ላይ ያሉ የእምነት ተቋማት ሁሉ ያለ ሥርዓት መቆም መኖር መገኘት አልቻሉም አይችሉምም ።

እያንዳንዱ የእምነት ተቋም በሕግና በሥርዓት የመኖሩ ጉዳይ አጠያያቂ አይደለም የአይሁድ እምነት ሥርዓትና ወግ ባህል ትውፊት ልዩ ቦታ የሚሰጠው በሰዎች ዘንድ ሁሉ የታወቀ ነበር ። ከክርስቶስ ልደት በኋላ ክርስትናው ሲመሠረትም ራሱን የቻለ የታወቀ ሕግና ሥርዓት አፈጻጸም ያለው ሆኖ ነው። ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች በጻፈው መልእክቱ (1ኛ ቆሮ 14÷40) ላይ ሁሉ በአግባብና በሥርዓት ይሁን ብሏል ይህም ማለት የአማንያኑ የእምነት አፈጻጸም ሕግና ሥርዓት ያለው መሆን እንዳለበትና በአግባቡ መፈጸም እንዳለበት ያስረዳናል ።

ማንኛውም የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚከናወንበት ሥርአት አለው ካህናቱ ሥርዓተ አምልኮውን (አግልግሎቱን) ሲፈጽሙ በሥርዓትና በአግባቡ መሆን እንዳለበት ምእመናኑም ለማገልገልም ሆነ ለመገልገል ሥርዓት እንደሚያስፈልግ ያስረዳል በየአብያተ ክርስቲያናቱ ዘንድ ልዩ የሚሆነው ጉዳይ ይኸ ሥርዓት አግባብ አለው ውይስ የለውም የሚለው ነው የተለያዩ የእምነት ድርጅቶች ስለ ሥርዓት እንኳን ያላቸው ግንዛቤ ከዚህ ግባ የማይባል እንደሆነ እያየን ነው። በዚህም ምክንያት እምነት በየጊዜው የሚለዋወጥ የተበከለ የተመረዘ ሕግንና ሥርዓትን ያልጠበቀ የቀደሙ አበው የሐዋርያት የሊቃውንትን አሰረ ፍኖት ያልተከተለ መሥመር የለቀቀ ሆኖ ይገኛል።

ቅዱስ ጳውሎስ በ2ኛ ተሰ 2÷15 ላይ “አሁንም ወንድሞቻችን ሆይ ጸንታችሁ ቁሙ በቃላችንም ቢሆን ወይም በመልእክታችን ያስተማርናችሁንና የሠራንላችሁን ሥርዓት ያዙ” በማለት አስረግጦ አስተምሮናል ስለሆነም ሥርአት ምንድን ነው ስንል በተፈጥሮ የተገኘና ፍጡራን በየጊዜው በዕለት ከዕለት ሕይወታቸው የሚፈጽሙት የእምነት ቀኖናቸውን የሚጠብቁበት እራሳቸውን የሚያዩበትና የሚመዝኑበት የሚያስተካክሉበት የሚገዙበት ስህተታቸውን የሚያርሙበት ድርጊት ነው ይህ ደግሞ ለሰው ልጆች ብቻ ሳይሆን ተንቀሳቃሽ ሕይወት ላላቸው እንስሳትም ሆነ ለሰማያውያን መላክት ጭምር በየድርሻቸው የተሠራና እስከ ምጽአት ድረስ የሚሠራ ነው።

በሥርዓትህ ለሚኖሩ እንስሳት ሁሉ ታጠግባለህ(መዝ 144÷16) ይሁን እንጅ ሥርዓትን ለመማር ሥርዓትን ለማወቅ ሥርዓትን ለመሥራት መጀመሪያውና ቀዳሚው ተግባር መጻሕፍትን ማንበብና መምህራንን መጠየቅ በዕውቀት ሙሉ ሆኖ መገኘት ሲሆን እነዚህንም ተግባራት ለማከናወን ይረዳን ዘንድ የደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶ ዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትሮንዳሔም ይህን ድረ ገጽ ሲያዘጋጅ ምእመናን የሚሰጠውን ትምህርት የሚተላለፈውን መልእክት አንብበው በትምህርቱ እራሳቸውን በዕውቀት ለማጠንከርና እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በምክረ ካህን በፈቃደ ካህን ለመኖር የሚረዳቸውን ዕውቀት የሚገበዩበት መንፈሳዊ የነፃ ገበያ እንዲሆን ታስቦ ነው። ስለሆነም የሚተላለፈውን መንፈሳዊ ምግብ በነፃ በመሸመት የመንፈሳዊ ሕይወት ረሀብ የያዛችሁ በድርቅ የተመታችሁ ሁሉ እንድታገግሙበት ቤተ ክርስቲያን አደራ ትላለች።

መጋቤ ብሉይ አባ ቀለመወርቅ አቡኔ
የቤተክርስቲያኑ አስተዳዳሪ

መንፈሳዊ አገልግሎት

የሰንበት ት/ቤት እና ህጻናት አገልግሎት

ያግኙን