• ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ!

  • "ድምፁ መልካም በሆነ ጸናጽል አመስግኑት፤ እልልታ ባለው ጸናጽል አመስግኑት" መዝ 150፥5

ዜናዎች እና ወቅታዊ ክንውኖች

የደብረ ታቦር በዓልና የጠቅላላ ጉባኤ አከባበር

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ የትሮንዳሔም ሰ/ት/ቤት ቀደም ብሎ በተያዘው ዓመታዊ መርሀ ግብር መሰረት የደብረ ታቦርን በዓል ከአባቶች ካህናት፣ በአካባቢው ከሚኖሩ ምእመናንና ምዕመናት ጋር በመሆን ነሐሴ ፲፩ ፳፻፭ ዓ.ም. በድምቀት አከበረ። በማግስቱ ነሐሴ ፲፪ ቀን ደግሞ አብላጫው የሰንበት ት/ቤቱ አባላት በተስማሙበት መሰረት ጠቅላላ ጉባኤ ተደርጐ የ ፮ ወር የአገልግሎት አፈጻጸምና ኦዲት ሪፖርቶች ቀርበው ጥልቅ ውይይት ተደርጎባቸዋል። […]

ስብከተ ወንጌልና ትምህርት በት/ሰ/ት/ቤት

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የትሮንዳሔም ሰንበት ትምህርት ቤት ከሀገር ቤት በመጡ መምህር ሰኔ ፳፪ እና ፳፫ ፳፻፭ ዓ.ም የስብከተ ወንጌል መርሃ ግብር በርካታ በአካባቢው የሚኖሩ ምእመናንና ምእመናት በተገኙበት ያካሄደ ሲሆን በተጨማሪም ከምዕመኑ ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሾችና ማብራሪያዎች ተሰጥቷል። ሰኔ ፳፬ እና ፳፭ ደግሞ አምስቱ አዕማደ ምስጢራተ ቤተክርስቲያን እና የስብከት ዘዴን በተመለከተ መጠነኛ ትምህርትና ስልጠና ተሰጥቷል። መርሃግብሩን […]

የትንሣኤ በዓል በደመቀ መልኩ ተከበረ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የትሮንዳሔም ሰንበት ትምህርት ቤት የትንሣኤንና የዳግም ትንሣኤን በዓላት ሚያዚያ ፳፯ እና ግንቦት ፫ ቀን ፳፻፭ ዓ።ም ከአባቶች ካህናት እና በአካባቢው ከሚኖሩ ምእመናንና ምእመናት ጋር አከበረ። የበዓሉን አከባበር በፎቶ ይመልከቱ

ትምህርታዊ ጽሑፎች

ትምህርተ ሃይማኖት ትምህርተ ሃይማኖት – ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማዕከል ትምህርተ ሃይማኖት – ማኅበረ ቅዱሳን አሜሪካ ማዕከል ልዩ ልዩ ሊቀ-ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ደብረ ዘይት “መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን፡- መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራሮች ናቸው” /መዝ.86፥1/ “የትንሣኤው ትርጉም በዓሉና አከባበሩ” “ፍኖተ መስቀል” ሰሙነ ሕማማት “ወደጄ ሆይ ተነሺ፣ ውበቴ ሆይ ነይ” (መኃ 2፡10) መንፈሳዊ ሕይወትና ስደት

የደብረዘይት በዓል በደመቀ መልኩ ተከበረ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የትሮንዳሔም ሰንበት ትምህርት ቤት የደብረዘይት በዓልን መጋቢት ፳፰ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም  ከአባቶች ካህናት እና በአካባቢው ከሚኖሩ ምእመናንና ምእመናት ጋር በድምቀት አከበረ። የበዓሉን አከባበር በፎቶ ይመልከቱ

በፌስቡክ ያግኙን

የአስተዳዳሪው መልእክት

ያለ ሥርዓት አልሄድንም  (2ኛ ተሰ 3÷7)

ማንኛውም ፍጡር በተፈጥሮ የተሰጠው ሕግና ሥርዓት አለው ይልቁንም ሰው የተፈጠረውና የሚኖረው ሲመራም የኖረበት ሥርዓት አለው። አፈጻጸማቸውና አጠቃቀማቸው ስለ ሥርዓትም ያላቸው ግንዛቤና የሚሰጡት ዋጋ የተለያየ ይሁን እንጅ በዓለም ላይ ያሉ የእምነት ተቋማት ሁሉ ያለ ሥርዓት መቆም መኖር መገኘት አልቻሉም አይችሉምም ።

እያንዳንዱ የእምነት ተቋም በሕግና በሥርዓት የመኖሩ ጉዳይ አጠያያቂ አይደለም የአይሁድ እምነት ሥርዓትና ወግ ባህል ትውፊት ልዩ ቦታ የሚሰጠው በሰዎች ዘንድ ሁሉ የታወቀ ነበር ። ከክርስቶስ ልደት በኋላ ክርስትናው ሲመሠረትም ራሱን የቻለ የታወቀ ሕግና ሥርዓት አፈጻጸም ያለው ሆኖ ነው። ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች በጻፈው መልእክቱ (1ኛ ቆሮ 14÷40) ላይ ሁሉ በአግባብና በሥርዓት ይሁን ብሏል ይህም ማለት የአማንያኑ የእምነት አፈጻጸም ሕግና ሥርዓት ያለው መሆን እንዳለበትና በአግባቡ መፈጸም እንዳለበት ያስረዳናል ።

ማንኛውም የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚከናወንበት ሥርአት አለው ካህናቱ ሥርዓተ አምልኮውን (አግልግሎቱን) ሲፈጽሙ በሥርዓትና በአግባቡ መሆን እንዳለበት ምእመናኑም ለማገልገልም ሆነ ለመገልገል ሥርዓት እንደሚያስፈልግ ያስረዳል በየአብያተ ክርስቲያናቱ ዘንድ ልዩ የሚሆነው ጉዳይ ይኸ ሥርዓት አግባብ አለው ውይስ የለውም የሚለው ነው የተለያዩ የእምነት ድርጅቶች ስለ ሥርዓት እንኳን ያላቸው ግንዛቤ ከዚህ ግባ የማይባል እንደሆነ እያየን ነው። በዚህም ምክንያት እምነት በየጊዜው የሚለዋወጥ የተበከለ የተመረዘ ሕግንና ሥርዓትን ያልጠበቀ የቀደሙ አበው የሐዋርያት የሊቃውንትን አሰረ ፍኖት ያልተከተለ መሥመር የለቀቀ ሆኖ ይገኛል።

ቅዱስ ጳውሎስ በ2ኛ ተሰ 2÷15 ላይ “አሁንም ወንድሞቻችን ሆይ ጸንታችሁ ቁሙ በቃላችንም ቢሆን ወይም በመልእክታችን ያስተማርናችሁንና የሠራንላችሁን ሥርዓት ያዙ” በማለት አስረግጦ አስተምሮናል ስለሆነም ሥርአት ምንድን ነው ስንል በተፈጥሮ የተገኘና ፍጡራን በየጊዜው በዕለት ከዕለት ሕይወታቸው የሚፈጽሙት የእምነት ቀኖናቸውን የሚጠብቁበት እራሳቸውን የሚያዩበትና የሚመዝኑበት የሚያስተካክሉበት የሚገዙበት ስህተታቸውን የሚያርሙበት ድርጊት ነው ይህ ደግሞ ለሰው ልጆች ብቻ ሳይሆን ተንቀሳቃሽ ሕይወት ላላቸው እንስሳትም ሆነ ለሰማያውያን መላክት ጭምር በየድርሻቸው የተሠራና እስከ ምጽአት ድረስ የሚሠራ ነው።

በሥርዓትህ ለሚኖሩ እንስሳት ሁሉ ታጠግባለህ(መዝ 144÷16) ይሁን እንጅ ሥርዓትን ለመማር ሥርዓትን ለማወቅ ሥርዓትን ለመሥራት መጀመሪያውና ቀዳሚው ተግባር መጻሕፍትን ማንበብና መምህራንን መጠየቅ በዕውቀት ሙሉ ሆኖ መገኘት ሲሆን እነዚህንም ተግባራት ለማከናወን ይረዳን ዘንድ የደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶ ዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትሮንዳሔም ይህን ድረ ገጽ ሲያዘጋጅ ምእመናን የሚሰጠውን ትምህርት የሚተላለፈውን መልእክት አንብበው በትምህርቱ እራሳቸውን በዕውቀት ለማጠንከርና እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በምክረ ካህን በፈቃደ ካህን ለመኖር የሚረዳቸውን ዕውቀት የሚገበዩበት መንፈሳዊ የነፃ ገበያ እንዲሆን ታስቦ ነው። ስለሆነም የሚተላለፈውን መንፈሳዊ ምግብ በነፃ በመሸመት የመንፈሳዊ ሕይወት ረሀብ የያዛችሁ በድርቅ የተመታችሁ ሁሉ እንድታገግሙበት ቤተ ክርስቲያን አደራ ትላለች።

መጋቤ ብሉይ አባ ቀለመወርቅ አቡኔ
የቤተክርስቲያኑ አስተዳዳሪ

መንፈሳዊ አገልግሎት

የሰንበት ት/ቤት እና ህጻናት አገልግሎት

ያግኙን