እንኳን ለዘመነ ማርቆስ በሰላምና በጤና አደረሳችሁ!

በትሮንዳሔም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ጊዮርጊስ ሰንበት ት/ርት ቤት የቅዱስ ዮሐንስን ዓመታዊ በዓል/ የ፳፻፮ ዓ.ም. የዘመን መለወጫን መስከረም ፩ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. በአካባቢው ከሚኖሩ ክርስቲያኖች ጋር በመሆን በዝማሬ እና በተለያዩ መንፈሳዊ ዝግጅቶች በድምቀት አከበረ። ዘመነ ማርቆስ የሰላም፣ የፍቅር፣ የጤና፣ የንስሐና የአገልግሎት ዘመን እንዲሆን የእግዚያብሔር ቅዱስ ፈቃድ ይሁንልን። አሜን።

ፎቶ ይመልከቱ

የደብረ ታቦር በዓልና የጠቅላላ ጉባኤ አከባበር

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ የትሮንዳሔም ሰ/ት/ቤት ቀደም ብሎ በተያዘው ዓመታዊ መርሀ ግብር መሰረት የደብረ ታቦርን በዓል ከአባቶች ካህናት፣ በአካባቢው ከሚኖሩ ምእመናንና ምዕመናት ጋር በመሆን ነሐሴ ፲፩ ፳፻፭ ዓ.ም. በድምቀት አከበረ። በማግስቱ ነሐሴ ፲፪ ቀን ደግሞ አብላጫው የሰንበት ት/ቤቱ አባላት በተስማሙበት መሰረት ጠቅላላ ጉባኤ ተደርጐ የ ፮ ወር የአገልግሎት አፈጻጸምና ኦዲት ሪፖርቶች ቀርበው ጥልቅ ውይይት ተደርጎባቸዋል።

የደብረ ታቦር በዓልንና ጠቅላላ ጉባኤ አከባበር በፎቶ ይመልከቱ

ስብከተ ወንጌልና ትምህርት በት/ሰ/ት/ቤት

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የትሮንዳሔም ሰንበት ትምህርት ቤት ከሀገር ቤት በመጡ መምህር ሰኔ ፳፪ እና ፳፫ ፳፻፭ ዓ.ም የስብከተ ወንጌል መርሃ ግብር በርካታ በአካባቢው የሚኖሩ ምእመናንና ምእመናት በተገኙበት ያካሄደ ሲሆን በተጨማሪም ከምዕመኑ ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሾችና ማብራሪያዎች ተሰጥቷል። ሰኔ ፳፬ እና ፳፭ ደግሞ አምስቱ አዕማደ ምስጢራተ ቤተክርስቲያን እና የስብከት ዘዴን በተመለከተ መጠነኛ ትምህርትና ስልጠና ተሰጥቷል።

መርሃግብሩን በፎቶ ይመልከቱ

የትንሣኤ በዓል በደመቀ መልኩ ተከበረ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የትሮንዳሔም ሰንበት ትምህርት ቤት የትንሣኤንና የዳግም ትንሣኤን በዓላት ሚያዚያ ፳፯ እና ግንቦት ፫ ቀን ፳፻፭ ዓ።ም ከአባቶች ካህናት እና በአካባቢው ከሚኖሩ ምእመናንና ምእመናት ጋር አከበረ።

የበዓሉን አከባበር በፎቶ ይመልከቱ

የደብረዘይት በዓል በደመቀ መልኩ ተከበረ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የትሮንዳሔም ሰንበት ትምህርት ቤት የደብረዘይት በዓልን መጋቢት ፳፰ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም  ከአባቶች ካህናት እና በአካባቢው ከሚኖሩ ምእመናንና ምእመናት ጋር በድምቀት አከበረ።

የበዓሉን አከባበር በፎቶ ይመልከቱ