በትሮንዳሔም የ ፩ ቀን ጉባኤ ተካሄደ
ለመንፈሳዊ አገልግሎት ከኢትዮጵያ ተጋብዘው ኖርዌይ በመጡት በዘማሪ ዲያቆን እንግዳወርቅ በቀለ እሁድ ህዳር ፳፰ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም በትሮንዳሔምና አካባቢው ለሚገኙ ምእመናን ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መዝሙርና ስብከተ ወንጌልን ያካተተ ጉባኤ አካሄደ።
ለመንፈሳዊ አገልግሎት ከኢትዮጵያ ተጋብዘው ኖርዌይ በመጡት በዘማሪ ዲያቆን እንግዳወርቅ በቀለ እሁድ ህዳር ፳፰ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም በትሮንዳሔምና አካባቢው ለሚገኙ ምእመናን ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መዝሙርና ስብከተ ወንጌልን ያካተተ ጉባኤ አካሄደ።
በቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በትሮንዳሔ በአካባቢው ለሚገኙ ምእመናን ለሦስት ተከታታይ ቀናት ከጥቅምት ፳፰ እስከ ፴ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም መንፈሳዊ ጉባኤ ተካሄደ። በጉባኤውም ላይ ቀሲስ ወንድወሰን ሶርሳን በመጋበዝ እምነት እና በዓለ መድኃኒዓለምን በተመለከተ ሰፋ ባለ መልኩ ትምህርተ ወንጌል ተሰጧል። ከምእመናን በቀረቡ ጥያቄዎች ላይ ማብራሪያ ከተሰጠ በኋላ መርሃ ግብሩ በሥርዓተ ጸሎት ተጠናቋል።
በቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትሮንዳሄም የመስቀል በዓል ዓርብ መስከረም ፲፮ ፳፻፯ ዓ.ም በስርዓተ ጸሎት፣ ደመራ በማብራት እና በያሬዳዊ ዝማሬ በየአመቱ እንደሚደረገው በመሆልት የተማሪዎች መኪና ማቆሚያ ቦታ ላይ ቀሲስ ተስፋዬ ፣ የደብሩ መዘምራንና በአካባቢው የሚኖሩ ምእመናንና ምእመናት በተገኙበት በዓሉ በድምቀት ተከበረ። ቀሲስ ተስፋዬ በዓሉን የሚመለከት ትምህርተ ወንጌል አስተላልፈዋል እንዲሁም የደብሩ መዘምራን የመዝሙር አገልግሎት አቅርበዋል።
በቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትሮንዳሄም የደብረ ታቦር በዓልና ጾመ ፍልሰታን ምክንያት በማድረግ ለ፪ ቀናት ማለትም ነሐሴ ፳፫ እና ፳፬ ፳፻፮ ዓ.ም የአካባቢው ምእመናንና ምእመናት በተገኙበት መንፈሳዊ ጉባኤ ተካሄደ። በጉባኤውም ላይ መላከ ጽዮን ቆሞስ አባ ሙሴ በመገኘት የስብከተ ወንጌል አገልግሎትና ስርዓተ ቅዳሴ እንዲከናወን በማድረግ በዓሉ በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል።
በቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትሮንዳሄም በመምህር ምሥጢረ ሥላሴ ማናዬ ከነሐሴ ፪ እስከ ፬ ፳፻፮ ዓ.ም መንፈሳዊ ጉባኤ ተካሄደ። በጉባኤውም ላይ በአካባቢው ለሚኖሩ ምእመናንና ምእመናት የሦስት ቀን የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ተካፋይ እንዲሆኑ ተደርጓል። ጉባኤውም በስርዓተ ጸሎት ተጀምሮ በእግዚአብሔር መልካም ፍቃድ በጸሎት ተጠናቋል።
የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ስቅለትና በዓለ ትንሣኤ በቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትሮንዳሔም አጥቢያ በሚገኙ ምእመናን እና ምእመናት በዕለቱ ተከብሮ ዋለ።
ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትሮንዳሔም የደብረዘይት በዓልን ከመጋቢት ፲፪ እስከ ፲፫፣ ፳፻፮ ዓ.ም. ከተለያዩ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት ከመጡ አባቶች ካህናት እና ወንድሞች ዲያቆናት እንዲሁም በአካባቢው ከሚኖሩ ምእመናንና ምእመናትጋር በቅዳሴ፣ በስብከተ ወንጌልና በያሬዳዊ ዝማሬ በታላቅ ድምቀት አከበረ።
ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትሮንዳሔም እሁድ ጥር ፲፰ ቀን ፳፻፮ ዓ. ም ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ። ጉባኤው በጸሎት ከተጀመረ በኋላ እ.ኤ.አ የ2013 እቅድ አፈጻጸምና የኦዲት ሪፖርት እንዲሁም የ2014/እ.ኤ.አ/ ዕቅድ ቀርቦ ሰፋ ያለ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ጸድቋል። ጉባኤው የተጀመረውን ዓመት በኃላፊነት ሊያገለግሉ የሚችሉ ሰባት መንፈሳዊ የሰበካ ጉባኤ አባላትን መርጦ ከአጸደቀ በኋላ በጸሎት ተዘግቷል።
በኖርዌይ በተለያዩ ከተማ የሚገኙት ስድስት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናት ማለትም የኦስሎ ቅዱስ ገብርኤል፤ የስታቫንጋር መድኃኔዓለም፤ የክርስቲያንሳንድ ቅድስት ድንግል ማርያም፤ የበርገን እመቤታችንና ቅዱስ ሚካኤል እና የትሮንዳሔም ቅዱስ ጊዮርጊስ ታቦታት አንድ ላይ በመሆን የጌታችን የአምላካችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን በዓለ ጥምቀት በበርገንበታላቅ ድምቀት አከበሩ። በዓሉ በኖርዌይና ከተለያዩ ሃገራት በመጡ አባቶች ካህናትና ምእመናን በተገኙበት በቤተ ክርስቲያናችን ስርዓት መሰረት ከከተራ ጀምሮ ማለትም ጥር ፲ እና ፲፩ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም በደማቅ መንፈሳዊ አገልግሎት ተከበረ። የጥምቀት በዓል በኖርዌይ በአንድነት መከበር የጀመረው በ፳፻፬ ዓ.ም በኦስሎ ከተማ ሲሆን እንደዚህ ቁጥራቸው በዛ ባሉ ታቦታት ሲከበር ግን የመጀመሪያ ነው። ይህ በዓል ባለፈው ዓመትም በስታቫንገር እንደዚሁ በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ እንደነበር ይታወሳል።