በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንየትሮንዳሔም ምሥራቀ ፀሐይ ቅ/ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ እኛ
  • የፎቶ ማኅደሮች
  • ያግኙን
  • Menu Menu

የ፳፻፰ ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል በደማቅ ሁኔታ ተከበረ

የቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትሮንዳሔም የ ፳፻፰ ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል ከኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በመጡ ካህናት እና መዘምራን፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትሮንዳሔም የሰንበት ት/ቤት መዘምራን፣ ከትሮንዳሔምና አካባቢው በተገኙ በርካታ ምእመናን እሁድ መስከረም ፲፮ በታላቅ ድምቀት ተከበረ።
በዓሉ እሁድ እለት ከሰዓት በኋላ በካህናት አባቶች ጸሎት የተጀመረ ሲሆን የቅዱስ ጊዮርጊስ አጥቢያ መዘምራን በዓሉን የተመለከቱ መዝሙራትን አቅርበዋል፣ የወንጌል ትምህርት ደግሞ ሥርዓተ ጸሎቱን በመሩት አባታችን ቀሲስ ተስፋዬ ከተሰጠ በኋላ በቅዱስ ሚካኤል የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መዘምራን እንዲሁ በዓሉን የሚያወድሱ ያሬዳዊ ዝማሬዎች ቀርበዋል።በማስከተልም ደመራው ተባርኮ የተለኮሰ ሲሆን መዘምራንና መላው ምእመንም በጋራ በመዘመር በዓሉን አድምቀውት አምሽተዋል፤በመጨረሻም ምእመናኑ ለበዓሉ የተዘጋጀውን ዝክር ቀምሰው ወደ የመጡበት በሰላም ተሸኝተዋል።
በዚሁ አጋጣሚ በተለያዩ መንገዶች ለዝግጅቱ መሳካት ብሎም ለበዓሉ ድምቀት ላደረጋችሁት መንፈሳዊ አስትዋጾ ሁሉ በሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ስም ልባዊ ምስጋና ማቅረብ እንወዳለን።

የበዓሉን ዝግጅት በፎቶ ይመልከቱ!

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotc-trondheim.no/a/wp-content/uploads/logo-trondheim.svg 0 0 tc https://eotc-trondheim.no/a/wp-content/uploads/logo-trondheim.svg tc2015-09-30 21:43:082018-10-11 14:45:16የ፳፻፰ ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል በደማቅ ሁኔታ ተከበረ
Search Search

በቅርብ ግዜ የተለቀቁ

  • የሊቀ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ የቅዳሴ ቤቱ ዓመታዊ ክብረ በዓል ህዳር ፮ እና ፯፥ ፳፻፲፰ ዓ.ም በድምቀት ተከበረ
  • ሊቀ-ሰማዕቱ-ቅዱስ-ጊዮርጊስ-ዓመታዊ-ክብረ በዓል (ህዳር) 2025
  • መስቀል – ፳፻፲፰ ዓ.ም.
  • መስቀል – ፳፻፲፰ ዓ.ም. — ፎቶ
  • አዲስ አመት – ፳፻፲፰ ዓ.ም.

በፌስቡክ ያግኙን

© ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትሮንዳሔም, St. George EOTC Trondheim , በአጥቢያ ዶት ኮም የተሰራ
ኢሜይል | አጥቢያ ፖርታል
Link to: የ፫ ቀናት መንፈሳዊ ጉባዔ ተካሄደ፤ የ፳፻፰ ዓ.ም ቅዱስ ዮሐንስ በዓልም በድምቀት ተከበረ Link to: የ፫ ቀናት መንፈሳዊ ጉባዔ ተካሄደ፤ የ፳፻፰ ዓ.ም ቅዱስ ዮሐንስ በዓልም በድምቀት ተከበረ የ፫ ቀናት መንፈሳዊ ጉባዔ ተካሄደ፤ የ፳፻፰ ዓ.ም... Link to: በቅዱስ ጊዮርጊስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በትሮንዳሄም ተከታታይ መንፈሳዊ ጉባዔ ተካሄደ Link to: በቅዱስ ጊዮርጊስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በትሮንዳሄም ተከታታይ መንፈሳዊ ጉባዔ ተካሄደ በቅዱስ ጊዮርጊስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በትሮንዳሄም ተከታታይ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top