• ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ!

  • "ድምፁ መልካም በሆነ ጸናጽል አመስግኑት፤ እልልታ ባለው ጸናጽል አመስግኑት" መዝ 150፥5

ዜናዎች እና ወቅታዊ ክንውኖች

ለ፪ ቀናት የቆየ ልዩ መንፈሳዊ ጉባዔ ተካሄደ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሰሜን ምዕራብ አውሮጳ ሃገረ ስብከት የትሮንዳሔም ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ለአገልግሎት ከኢትዮጵያ ወደ አውሮጳ በመጡት በኩረ መዘምራን ኪነጥበብ ወ/ቂርቆስ እና መጋቤ ሐዲስ ምሥጢረ ሥላሴ ማናዬ ለ፪ ቀናት የቆየ የዝማሬና የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ተካሄደ። ጉባዔው ከትሮንዳሔምና አካባቢው በተገኙ ምዕመናን ቅዳሜ መስከረም ፳፰ በ 9:00 ሰዓት እንዲሁም መስከረም ፳፱ በ 10:30 ሰዓት ስለሃገራችን ሰላምና መረጋጋት የዘወትርና […]

የ ፳፻፱ ዓ.ም መስቀል ደመራ በዓል በድምቀት ተከበረ፤ የ፫ ቀናት መንፈሳዊ ጉባዔም ተካሄደ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሰሜን ምዕራብ አውሮጳ ሃገረ ስብከት የትሮንዳሔም ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ለአገልግሎት ከኢትዮጵያ ወደ አውሮጳ በመጡትና ወደ አጥቢያችን የመስቀልን በዓል ለማክበር በተጋበዙት መምህር ፍቃዱ ሳህሌ የ፫ ቀናት ጉባዔ ተካሄደ። ቅዳሜ፣ እሁድ እንዲሁም ማክሰኞ (ከመስከረም ፲፬ – ፲፯) በተካሄደው ጉባዔ ላይ በተለያዩ ርዕሶች መንፈሳዊ ትምህርት ለትሮንዳሔምና አካባቢው ምዕመናን የተሰጠ ሲሆን ከምዕመናን በተነሱ ጥያቄዎች ላይ ምላሽና ምክረ […]

የ፳፻፰ ዓ.ም የፍልሰታ ለማርያም ጾም አጋማሽ ቅዳሴና የአንድ ቀን ጉባኤ ተካሄደ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/በሰሜን ምዕራብ አውሮጳ ሀ/ስብከት የትሮንዳሔም ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ቅዳሜ ነሐሴ ፯፥፳፻፰ ዓ.ም ከኢትዮጵያ በመጡት ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ (ሊቀ መዘምር) የፍልሰታን ጾም በማስመልከት የቅዳሴ መርሐ ግብር የተከናወነ ሲሆን ከቅዳሴው በኋላ በአጥቢያው ሕጻናት አጫጭር መዝሙራት ቀርበዋል። ። በመቀጠልም በቀሲስ ምንዳዬ ዝማሬዎችና ዕለቱን የተመለከተ የወንጌል ትምህርት ተሰጥቷል። በመጨረሻም የዕለቱ መርሐ ግብር በአባታችን ቡራኬ ተፈጽሟል። በነጋታው እሁድ ነሐሴ ፰፥ […]

ልዩ መንፈሳዊ የሕፃናት ቀን በአጥቢያችን በታላቅ ድምቀት ተከበረ

በአይነቱ ልዩ የሆነና ሕጻናትን ያማከለ መርሐ ግብር በአጥቢያችን የቅዱስ ጊዮርጊስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በትሮንዳሄም ሰኔ ፲፪፥ ፳፻፰ ዓ.ም (June 19, 2016) ተካሄደ። የዕለቱ ዝግጅት በጸሎት ከተጀመረ በኋላ ሕፃን ሕርያቆስ እና ሕፃን ሊድያ በጋራ በመሆን በጣፋጭ የሕፃን አንደበታቸው አባታችን ሆይ በማድረስ የሕጻናቱ መርሐ ግብር በይፋ የተጀመረ ሲሆን የምሥጢራት ሁሉ መጀመርያ የሆነው ምሥጢረ ሥላሴን ሕፃን ሔርሜላ፣ ሕፃን ማሪያና፣ ሕፃን […]

የ፳፻፰ ዓ.ም ጰራቅሊጦስ በዓል በድምቀት ተከበረ

በቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትሮንዳሔም የ፳፻፰ ዓ.ም ጰራቅሊጦስ በዓል ሰኔ ፲፩፥፳፻፰ ዓ.ም (June 18, 2016) በቅዳሴ፣ በያሬዳዊ ዝማሬዎችና በስብከት ተከበረ። በዕለቱ ከዴንማርክ የተጋብዙት አባ ዘሚካኤል ዴሬሳ ፣ ከቅዱስ ሚካኤል የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዲያቆናት እንዲሁም በትሮንዳሄምና አካባቢው የሚኖሩ ምእመናን የተገኙ ሲሆን መርሐ ግብሩ ከንጋቱ 12:30 (06:30AM) ሰዓት በጸሎትና በምንባባት ከተጀመረ በኋላ በቅዳሴ […]

በፌስቡክ ያግኙን

የአስተዳዳሪው መልእክት

ያለ ሥርዓት አልሄድንም  (2ኛ ተሰ 3÷7)

ማንኛውም ፍጡር በተፈጥሮ የተሰጠው ሕግና ሥርዓት አለው ይልቁንም ሰው የተፈጠረውና የሚኖረው ሲመራም የኖረበት ሥርዓት አለው። አፈጻጸማቸውና አጠቃቀማቸው ስለ ሥርዓትም ያላቸው ግንዛቤና የሚሰጡት ዋጋ የተለያየ ይሁን እንጅ በዓለም ላይ ያሉ የእምነት ተቋማት ሁሉ ያለ ሥርዓት መቆም መኖር መገኘት አልቻሉም አይችሉምም ።

እያንዳንዱ የእምነት ተቋም በሕግና በሥርዓት የመኖሩ ጉዳይ አጠያያቂ አይደለም የአይሁድ እምነት ሥርዓትና ወግ ባህል ትውፊት ልዩ ቦታ የሚሰጠው በሰዎች ዘንድ ሁሉ የታወቀ ነበር ። ከክርስቶስ ልደት በኋላ ክርስትናው ሲመሠረትም ራሱን የቻለ የታወቀ ሕግና ሥርዓት አፈጻጸም ያለው ሆኖ ነው። ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች በጻፈው መልእክቱ (1ኛ ቆሮ 14÷40) ላይ ሁሉ በአግባብና በሥርዓት ይሁን ብሏል ይህም ማለት የአማንያኑ የእምነት አፈጻጸም ሕግና ሥርዓት ያለው መሆን እንዳለበትና በአግባቡ መፈጸም እንዳለበት ያስረዳናል ።

ማንኛውም የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚከናወንበት ሥርአት አለው ካህናቱ ሥርዓተ አምልኮውን (አግልግሎቱን) ሲፈጽሙ በሥርዓትና በአግባቡ መሆን እንዳለበት ምእመናኑም ለማገልገልም ሆነ ለመገልገል ሥርዓት እንደሚያስፈልግ ያስረዳል በየአብያተ ክርስቲያናቱ ዘንድ ልዩ የሚሆነው ጉዳይ ይኸ ሥርዓት አግባብ አለው ውይስ የለውም የሚለው ነው የተለያዩ የእምነት ድርጅቶች ስለ ሥርዓት እንኳን ያላቸው ግንዛቤ ከዚህ ግባ የማይባል እንደሆነ እያየን ነው። በዚህም ምክንያት እምነት በየጊዜው የሚለዋወጥ የተበከለ የተመረዘ ሕግንና ሥርዓትን ያልጠበቀ የቀደሙ አበው የሐዋርያት የሊቃውንትን አሰረ ፍኖት ያልተከተለ መሥመር የለቀቀ ሆኖ ይገኛል።

ቅዱስ ጳውሎስ በ2ኛ ተሰ 2÷15 ላይ “አሁንም ወንድሞቻችን ሆይ ጸንታችሁ ቁሙ በቃላችንም ቢሆን ወይም በመልእክታችን ያስተማርናችሁንና የሠራንላችሁን ሥርዓት ያዙ” በማለት አስረግጦ አስተምሮናል ስለሆነም ሥርአት ምንድን ነው ስንል በተፈጥሮ የተገኘና ፍጡራን በየጊዜው በዕለት ከዕለት ሕይወታቸው የሚፈጽሙት የእምነት ቀኖናቸውን የሚጠብቁበት እራሳቸውን የሚያዩበትና የሚመዝኑበት የሚያስተካክሉበት የሚገዙበት ስህተታቸውን የሚያርሙበት ድርጊት ነው ይህ ደግሞ ለሰው ልጆች ብቻ ሳይሆን ተንቀሳቃሽ ሕይወት ላላቸው እንስሳትም ሆነ ለሰማያውያን መላክት ጭምር በየድርሻቸው የተሠራና እስከ ምጽአት ድረስ የሚሠራ ነው።

በሥርዓትህ ለሚኖሩ እንስሳት ሁሉ ታጠግባለህ(መዝ 144÷16) ይሁን እንጅ ሥርዓትን ለመማር ሥርዓትን ለማወቅ ሥርዓትን ለመሥራት መጀመሪያውና ቀዳሚው ተግባር መጻሕፍትን ማንበብና መምህራንን መጠየቅ በዕውቀት ሙሉ ሆኖ መገኘት ሲሆን እነዚህንም ተግባራት ለማከናወን ይረዳን ዘንድ የደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶ ዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትሮንዳሔም ይህን ድረ ገጽ ሲያዘጋጅ ምእመናን የሚሰጠውን ትምህርት የሚተላለፈውን መልእክት አንብበው በትምህርቱ እራሳቸውን በዕውቀት ለማጠንከርና እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በምክረ ካህን በፈቃደ ካህን ለመኖር የሚረዳቸውን ዕውቀት የሚገበዩበት መንፈሳዊ የነፃ ገበያ እንዲሆን ታስቦ ነው። ስለሆነም የሚተላለፈውን መንፈሳዊ ምግብ በነፃ በመሸመት የመንፈሳዊ ሕይወት ረሀብ የያዛችሁ በድርቅ የተመታችሁ ሁሉ እንድታገግሙበት ቤተ ክርስቲያን አደራ ትላለች።

መጋቤ ብሉይ አባ ቀለመወርቅ አቡኔ
የቤተክርስቲያኑ አስተዳዳሪ

መንፈሳዊ አገልግሎት

የሰንበት ት/ቤት እና ህጻናት አገልግሎት

ያግኙን