በትሮንዳሔም የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ተቋቋመ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የትሮንዳሔም ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰንበት ት/ቤት ከ 17 ዓመታት ጉዞ በኋላ ወደ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አደገ። ሰንበት ትምህርት ቤቱ እ.ኤ.አ በ 1995 «በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የትሮንዳሔም ሰንበት ት/ቤት» ተብሎ የተመሰረተ ሲሆን አሁን ቅዱስ እግዚአብሔር ፈቅዶ ታቦተ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ በሊቃነ ጳጳሳት ተባርኮ በመጋቢ ምስጢር ቆሞስ አባ ቴዎድሮስ አማካኝነት ወደ ኖርዌይ በመምጣቱ ወደ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ሊያድግ ችሏል። አጥቢያ ቤተ ክርስቲያኑን ማቋቋም አስመልክቶ የሁለት ቀን ጉባኤ ታህሳስ ፬ እና ፭ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም ተዘጋጅቶ ታቦተ ሕጉን በደማቅ ስነ ሥርዓት ከተቀበልን በኋላ በሥርዓተ ጸሎት በትሮንዳሔም የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ተቋቋመ። Read more