በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንየትሮንዳሔም ምሥራቀ ፀሐይ ቅ/ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ እኛ
  • የፎቶ ማኅደሮች
  • ያግኙን
  • Menu Menu

ቤተ ክርስቲያናችን መንበረ ፕትርክናው ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ስር በአስተዳደራዊ መዋቅር መታቀፏን ስለማሳዎቅ

letter1 107x151ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅድመ ታሪኩ እ.ኤ.አ በ1995 መጨረሻ ላይ ለትምህርት ወደ ትሮንዳሄም፣ ኖርዌይ በመጡ ቀናኢ የቤተክርስቲያን ልጆች አማካኝነት በሰንበት ትምህርት ቤትነት ደረጃ በመቋቋም ነበር። ሰንበት ት/ቤት በነበረበት ወቅት እ.ኤ.አ በ2010 ህጋዊ ሆኖ በኖርዌይ ሀገር በሃይማኖት ተቋምነት የተመዘገበ ሲሆን ቅዱስ ጊዮርጊስ በመባል እ.ኤ.አ በ2012 በአቅራቢያው እየመጡ በሚያገለግሉን አባቶች ተሰይሟል። እ.ኤ.አ በ2013 ደግሞ ታቦተ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ በአባቶች ተባርኮ መጥቶ ከሰንበት ትምህርት ቤትነት ወደ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያንነት በማደግ ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተመስርቷል። በዚህ ጉዞዋ ቤተ ክስቲያናችን በዚህ መዋቅር ነኝ ብላ ባታውጅም፤ ከአባቶቻችን እንደተማርነው ያለመዋቅርና ያለስርዓት መጓዝ ጥሩና አግባብ ባለመሆኑ /መዝ. ፻፲፰፥፻፲፰ ፡ ፩ኛ ተሰ. ፭፥፲፬ ፡ ፪ኛ ተሰ. ፫፥፮/ አጥቢያችን በአስተዳደራዊ መዋቅር ስር ገብታ ትተዳደር ዘንድ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያናዊና ሀይማኖታዊ ህግ መሆኑ ግልጽ ነው። ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤው ይህን ሃይማኖታዊ ስርዓት ሰፊ ጊዜ በመውሰድ የተወያየበት ሲሆን ከአባቶችም ጋር እንደዚሁ በተለያዩ ጊዜያት ውይይት አድርጓል። ከዚህም በተጨማሪ ምዕመናን በጉዳዩ ዙርያ ሰፊ ግንዛቤ እንዲኖራቸውና ይህን አጀንዳ በሃይማኖትና በእምነት መነጸር ብቻ እንዲመለከቱት የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ትምህርት እና ቅዱስ ሲኖዶስ ለቤተ ክርስቲያን መተዳደርያ ህግ ይሆን ዘንድ ባወጣው ቃለ ዓዋዲ ላይ ሰፊ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ጥረት ተደርጓል።

 

ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ህግ አንፃር፣ እንዲሁም ይህች ቤተ ክርስቲያናችን ስትመሰረት ታቦተ ህጋችን በብፁዓን አባቶች ተባርኮ ከሀገር ቤት እንደመምጣቱ መጠን፤ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤው ነገሮችን በእርጋታ ተመልክቶ የትሮንዳሔም ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶስ ስር እንድትሆን አቅጣጫ አስቀምጦ ለተግባራውነቱ በእግዚአብሔር መልካም ፍቃድ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል። በዚህም መሰረት በጉዳይ ላይ ከምዕመኑ ጋር ለመነጋገር ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤው ኅዳር ፳፭፥ ፳፻፰ ዓ.ም ልዩ ጠቅላላ ጉባኤ ጠርቶ ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን በትሮንዳሔም የቤተ ክርስትያን መዋቅርና የቤተ ክርስቲያኗን የበላይ ጠባቂ በግልጽ ስለ ማሳወቅ በሚል ርዕስ አባቶች በተገኙበት አወያይቷል። በዕለቱም ስለሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ትምህርት እንዲሁም ስለቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን በትሮንዳሔም የቤተ ክርስቲያን መዋቅር ጉዳይ ገለፃ ተሰጥቶ ግልፅ ውይይት ተደርጓል። ጠቅላላ ጉባኤውም የትሮንዳሔም ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፕትርክናው ኢትዮጵያ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶስ ስር ቤተ ክርስቲያናዊ መዋቅርን ጠብቃና አክብራ መተዳደር አለባት በማለት ምልዓተ ጉባኤው ወስኗል።

 

 በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ መዋቅር ስር መሆናችንን ስለማሳወቅ ለብጹዕ አቡነ እንጦንስ ለሰ/ሰ/ምዕ/ አውሮፓ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ የተጻፈ ደብዳቤ።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotc-trondheim.no/a/wp-content/uploads/logo-trondheim.svg 0 0 tc https://eotc-trondheim.no/a/wp-content/uploads/logo-trondheim.svg tc2015-12-19 22:01:202015-12-19 22:01:20ቤተ ክርስቲያናችን መንበረ ፕትርክናው ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ስር በአስተዳደራዊ መዋቅር መታቀፏን ስለማሳዎቅ
Search Search

በቅርብ ግዜ የተለቀቁ

  • የሊቀ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ የቅዳሴ ቤቱ ዓመታዊ ክብረ በዓል ህዳር ፮ እና ፯፥ ፳፻፲፰ ዓ.ም በድምቀት ተከበረ
  • ሊቀ-ሰማዕቱ-ቅዱስ-ጊዮርጊስ-ዓመታዊ-ክብረ በዓል (ህዳር) 2025
  • መስቀል – ፳፻፲፰ ዓ.ም.
  • መስቀል – ፳፻፲፰ ዓ.ም. — ፎቶ
  • አዲስ አመት – ፳፻፲፰ ዓ.ም.

በፌስቡክ ያግኙን

© ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትሮንዳሔም, St. George EOTC Trondheim , በአጥቢያ ዶት ኮም የተሰራ
ኢሜይል | አጥቢያ ፖርታል
Link to: በቅዱስ ጊዮርጊስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በትሮንዳሄም ተከታታይ መንፈሳዊ ጉባዔ ተካሄደ Link to: በቅዱስ ጊዮርጊስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በትሮንዳሄም ተከታታይ መንፈሳዊ ጉባዔ ተካሄደ በቅዱስ ጊዮርጊስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በትሮንዳሄም ተከታታይ... Link to: የ፳፻፰ ዓ.ም የልደት በዓል በድምቀት ተከበረ Link to: የ፳፻፰ ዓ.ም የልደት በዓል በድምቀት ተከበረ የ፳፻፰ ዓ.ም የልደት በዓል በድምቀት ተከበረ
Scroll to top Scroll to top Scroll to top