በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንየትሮንዳሔም ምሥራቀ ፀሐይ ቅ/ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ እኛ
  • የፎቶ ማኅደሮች
  • ያግኙን
  • Menu Menu

የሊቀ ሰማዕታቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ ክብረ በዓል በደመቀ መልኩ ተከበረ

በቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትሮንዳሔም የሚያዝያ ፳፫፣ ፳፻፯ ዓ.ም የሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ ክብረ በዓል ከተለያዩ አውሮፓ ሀገራት ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ተጋብዘው በመጡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ የሰንበት ት/ቤት መዘምራን፣ ከመላው ኖርዌይ እንዲሁም ከትሮንዳሔምና አካባቢው በተገኙ ምእመናን ዓርብ ሚያዚያ ፳፫ እና ቅዳሜ ሚያዚያ ፳፬ በታላቅ ድምቀት ተከበረ።

በዓሉ ዓርብ እለት ከሰዓት በኋላ በጸሎት የተጀመረ ሲሆን ስለ ቅዱስ ያሬድ በሊቀ ጠበብት ተክሌ ሲራክ፣ የወንጌል ትምህርት ደግሞ በዲያቆን ብሩክ አሸናፊ ከተሰጠ በኋላ በቅዱስ ጊዮርጊስ አጥቢያ መዘምራን፣ በቅዱስ ሚካኤል የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መዘምራን እንዲሁም በዲያቆን ብሩክ በአሉን የሚያወድሱ ያሬዳዊ ዝማሬዎች ቀርበዋል። በመጨረሻም የማሳረጊያ ትምህርት በመጋቤ ምስጢር ቆሞስ አባ ቴዎድሮስ ተሰጥቶ የዓርብ ከሰአቱ ጉባኤ በጸሎት ተፈጽሟል።

በመቀጠልም ጉባኤው ዓርብ ለቅዳሜ ሌሊቱን በሊቀ ጠበብት ተክሌ ሲራክ መሪነት በአባቶች፣ ዲያቆናት፣ የሰ/ት/ ቤት መዘምራንና በምእመናን ተሳትፎ የቅኔ ማሕሌቱ ስርዓት በደመቀ መልኩ ተከናውኗል። እንዲሁም የነግህ ኪዳንና የቅዳሴው ስርዓት ሲጠናቀቅ በአጥቢያው መዘምራንና በዲያቆንብሩክ አሸናፊ ያሬዳዊ መዝሙር ከቀረበ በኋላ የዕለቱ ስብከተ ወንጌል በመልዓከ ጽዮን ቆሞስ አባ ሙሴተሰጥቷል። ከእለቱ ትምህርት በኋላ የቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ በዓል ስርዓተ-ንግስ በደመቀ ሁኔታ ተከናውኗል።

በመጨረሻም በአባቶች በቅርቡ ስለእምነታቸው ሰማዕት ለሆኑ ክርስቲያኖች ጸሎት ካደረሱ እና ምዕመኑ ጧፍ በማብራት እንዲታሰቡ ከተደረገ በኋላ ታቦተ ህጉ ወደመንበረ ክብሩ ተመልሷል። ምእመናንም ለበዓሉ የተዘጋጀውን ዝክር ቀምሰው ወደየመጡበት በሰላም ተሸኝተዋል።

በዚሁ አጋጣሚ በተለያዩ መንገዶች ለዝግጅቱ መሳካት ብሎም ለበዓሉ ድምቀት ላደረጋችሁት መንፈሳዊ አስትዋጾ ሁሉ በሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ስም ልባዊ ምስጋና ማቅረብ እንወዳለን።

የበዓሉን ዝግጅት በፎቶ ይመልከቱ!

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotc-trondheim.no/a/wp-content/uploads/logo-trondheim.svg 0 0 tc https://eotc-trondheim.no/a/wp-content/uploads/logo-trondheim.svg tc2015-05-05 19:01:402018-10-11 14:45:16የሊቀ ሰማዕታቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ ክብረ በዓል በደመቀ መልኩ ተከበረ
Search Search

በቅርብ ግዜ የተለቀቁ

  • የሊቀ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ የቅዳሴ ቤቱ ዓመታዊ ክብረ በዓል ህዳር ፮ እና ፯፥ ፳፻፲፰ ዓ.ም በድምቀት ተከበረ
  • ሊቀ-ሰማዕቱ-ቅዱስ-ጊዮርጊስ-ዓመታዊ-ክብረ በዓል (ህዳር) 2025
  • መስቀል – ፳፻፲፰ ዓ.ም.
  • መስቀል – ፳፻፲፰ ዓ.ም. — ፎቶ
  • አዲስ አመት – ፳፻፲፰ ዓ.ም.

በፌስቡክ ያግኙን

© ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትሮንዳሔም, St. George EOTC Trondheim , በአጥቢያ ዶት ኮም የተሰራ
ኢሜይል | አጥቢያ ፖርታል
Link to: ሊቀ-ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ Link to: ሊቀ-ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ-ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ Link to: የ፫ ቀናት መንፈሳዊ ጉባዔ ተካሄደ፤ የ፳፻፰ ዓ.ም ቅዱስ ዮሐንስ በዓልም በድምቀት ተከበረ Link to: የ፫ ቀናት መንፈሳዊ ጉባዔ ተካሄደ፤ የ፳፻፰ ዓ.ም ቅዱስ ዮሐንስ በዓልም በድምቀት ተከበረ የ፫ ቀናት መንፈሳዊ ጉባዔ ተካሄደ፤ የ፳፻፰ ዓ.ም...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top