በሀገረ ኖርዌይ በትሮንድሃይም በምሥራቀ ፀሐይ ቀዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያ የመስቀል ደመራ በዓል በደማቅ ሁኔታ ተከበረ
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ አደረሰን ።
“ዝንቱ መስቀል ቤዛነ መድኃኒት ለአሕዛብ ስደተ ኮነ ወለነኒ ሕይወተ ኮነነ ፣ ለአሕዛብ ስደት የሆነው ለኛ ግን ሕይወት የሆነን ይህ መስቀል ቤዛችን መድኃኒታችን ነው” ቅዱስ ያሬድ።
መስከረም 16 2019 የመስቀል ደመራ በዓል በሀገረ ኖርዌይ በትሮንድሃይም በምሥራቀ ፀሐይ ቀዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ከኤርትራውያን ወንድሞቻችን ጋራ በመሆን በድምቀት ተከበረ።
ይችን ጊዜ ለሰጠን የጊዜ ባለቤት አምላከ ቅዱሳን ስሙ ይክበር ይመስገን አሜን!!!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።