በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንየትሮንዳሔም ምሥራቀ ፀሐይ ቅ/ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ እኛ
  • የፎቶ ማኅደሮች
  • ያግኙን
  • Menu Menu

ልዩ መንፈሳዊ የሕፃናት ቀን በአጥቢያችን በታላቅ ድምቀት ተከበረ

በአይነቱ ልዩ የሆነና ሕጻናትን ያማከለ መርሐ ግብር በአጥቢያችን የቅዱስ ጊዮርጊስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በትሮንዳሄም ሰኔ ፲፪፥ ፳፻፰ ዓ.ም (June 19, 2016) ተካሄደ።

የዕለቱ ዝግጅት በጸሎት ከተጀመረ በኋላ ሕፃን ሕርያቆስ እና ሕፃን ሊድያ በጋራ በመሆን በጣፋጭ የሕፃን አንደበታቸው አባታችን ሆይ በማድረስ የሕጻናቱ መርሐ ግብር በይፋ የተጀመረ ሲሆን የምሥጢራት ሁሉ መጀመርያ የሆነው ምሥጢረ ሥላሴን ሕፃን ሔርሜላ፣ ሕፃን ማሪያና፣ ሕፃን ቢቲ እና ሕፃን ቲና በመቀባበል በምልልስ መልኩ በዜማ አቅርበዋል። በማስከተልም የዕለቱን ክፍል አንድ ትምህርት ሕፃን ሔርሜላ የአባታችን የኖኅን ታሪክ በመተረክ ስለኃጢያት አስከፊነትና ለእግዚአብሔር ስለመታዘዝ አጠር ያለ ትምህርት አቅርባለች። ከዚያም በመቀጠል ሁሉም ሕፃናት ዓውደ ምህረቱ ላይ “ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ” እንደተባለ ጣፋጭ ዝማሬዎችን አከታትለው አቅርበዋል።

በክፍል ሁለት ሕፃን ቢቲ በነብዩ ዮናስ ታሪክ ላይ ተመስርታ ስለ እግዚአብሔር መሃሪነት፣ ለፍጥረቱ ያለውን ፍቅር፣ ለእርሱ ስለመታዘዝ አስፈላጊነት የሚያስረዳ ትምህርት አዘል ጽሁፍ አቅርባለች። ቀጣዩ የጥያቄና መልስ መርሐ ግብርም በዓሉን ለመታደም ከላቫንገር ከተማ ለመጡት ሕፃን ዳግማዊ እና ሕፃን ካሌብ ቀርቦ ሕጻናቱ የቀረቡላቸውን ሃይማኖታዊ ጥያቄዎች በሙሉ በመመለስ ምዕመናንን አስገርመዋል።

በመቀጠልም ለሕፃናት የምሳ ግብዣ ተካሂዶ ለወላጆች በልጆች አስተዳደግ ዙርያ አጠር ያለ ገለጻ ከቀረበ በኋላ በጉዳዩ ላይ መልካም ተሞክሮ ያላቸው ወላጆች ልምድ በቃለ መጠይቅ መልክ ቀርቧል።

በመጨረሻም በዕለቱ ለተገኙት ሁሉም ሕጻናት ስጦታ ተሰጥቶ መርሐ ግብሩ በጸሎት ተደምድሟል። ምዕመናንም የተዘጋጀውን ጸበል ጸዲቅ ቀመሰው በሰላም ወደየቤታቸው ተመልሰዋል።

የበዓሉን አከባበር በፎቶ ይመልከቱ!

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotc-trondheim.no/a/wp-content/uploads/logo-trondheim.svg 0 0 tc https://eotc-trondheim.no/a/wp-content/uploads/logo-trondheim.svg tc2016-06-22 15:31:572018-10-11 14:45:17ልዩ መንፈሳዊ የሕፃናት ቀን በአጥቢያችን በታላቅ ድምቀት ተከበረ
Search Search

በቅርብ ግዜ የተለቀቁ

  • የሊቀ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ የቅዳሴ ቤቱ ዓመታዊ ክብረ በዓል ህዳር ፮ እና ፯፥ ፳፻፲፰ ዓ.ም በድምቀት ተከበረ
  • ሊቀ-ሰማዕቱ-ቅዱስ-ጊዮርጊስ-ዓመታዊ-ክብረ በዓል (ህዳር) 2025
  • መስቀል – ፳፻፲፰ ዓ.ም.
  • መስቀል – ፳፻፲፰ ዓ.ም. — ፎቶ
  • አዲስ አመት – ፳፻፲፰ ዓ.ም.

በፌስቡክ ያግኙን

© ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትሮንዳሔም, St. George EOTC Trondheim , በአጥቢያ ዶት ኮም የተሰራ
ኢሜይል | አጥቢያ ፖርታል
Link to: የ፳፻፰ ዓ.ም ጰራቅሊጦስ በዓል በድምቀት ተከበረ Link to: የ፳፻፰ ዓ.ም ጰራቅሊጦስ በዓል በድምቀት ተከበረ የ፳፻፰ ዓ.ም ጰራቅሊጦስ በዓል በድምቀት ተከበ... Link to: የ፳፻፰ ዓ.ም የፍልሰታ ለማርያም ጾም አጋማሽ ቅዳሴና የአንድ ቀን ጉባኤ ተካሄደ Link to: የ፳፻፰ ዓ.ም የፍልሰታ ለማርያም ጾም አጋማሽ ቅዳሴና የአንድ ቀን ጉባኤ ተካሄደ የ፳፻፰ ዓ.ም የፍልሰታ ለማርያም ጾም አጋማሽ ቅዳሴና...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top