በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንየትሮንዳሔም ምሥራቀ ፀሐይ ቅ/ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ እኛ
  • የፎቶ ማኅደሮች
  • ያግኙን
  • Menu Menu

የ፳፻፰ ዓ.ም የፍልሰታ ለማርያም ጾም አጋማሽ ቅዳሴና የአንድ ቀን ጉባኤ ተካሄደ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/በሰሜን ምዕራብ አውሮጳ ሀ/ስብከት የትሮንዳሔም ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ቅዳሜ ነሐሴ ፯፥፳፻፰ ዓ.ም ከኢትዮጵያ በመጡት ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ (ሊቀ መዘምር) የፍልሰታን ጾም በማስመልከት የቅዳሴ መርሐ ግብር የተከናወነ ሲሆን ከቅዳሴው በኋላ በአጥቢያው ሕጻናት አጫጭር መዝሙራት ቀርበዋል። ። በመቀጠልም በቀሲስ ምንዳዬ ዝማሬዎችና ዕለቱን የተመለከተ የወንጌል ትምህርት ተሰጥቷል። በመጨረሻም የዕለቱ መርሐ ግብር በአባታችን ቡራኬ ተፈጽሟል።

በነጋታው እሁድ ነሐሴ ፰፥ ዓ.ም ረፋድ ላይ የዕለቱ መርሐ ግብር ኪዳን በማድረስ የተጀመረ ሲሆን በመቀጠልም ቀሲስ ምንዳዬ ተከታታይ ዝማሬዎችን ካቀረቡ በኋላ የዕለቱ የወንጌል ትምህርት በወንድም ኃይሉ (ዶ/ር) ስለጾም አስፈላጊነት ሰፋ ያለ ትምህርት ተሰጥቷል። በስተመጨረሻም በቀሲስ ምንዳዬ የማጠቃለያ ትምህርትና ተጨማሪ ዝማሬዎች ተዘምረው የዕለቱ መርሐ ግብር በጸሎት ተፈጽሟል። በዕለቱ የተገኙት ምዕመናንም ከቀሲስ ምንዳዬ ጋር የማስታወሻ ፎቶ ተነስተው በዕለቱ የተዘጋጀውን ጸበል ጸዲቅ ቀምሰው ወደየቤታቸው በሰላም ተመልሰዋል።

መርሐ ግብሩን በምስል ይመልከቱ !

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotc-trondheim.no/a/wp-content/uploads/logo-trondheim.svg 0 0 tc https://eotc-trondheim.no/a/wp-content/uploads/logo-trondheim.svg tc2016-08-23 20:28:182018-10-11 14:45:17የ፳፻፰ ዓ.ም የፍልሰታ ለማርያም ጾም አጋማሽ ቅዳሴና የአንድ ቀን ጉባኤ ተካሄደ
Search Search

በቅርብ ግዜ የተለቀቁ

  • የሊቀ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ የቅዳሴ ቤቱ ዓመታዊ ክብረ በዓል ህዳር ፮ እና ፯፥ ፳፻፲፰ ዓ.ም በድምቀት ተከበረ
  • ሊቀ-ሰማዕቱ-ቅዱስ-ጊዮርጊስ-ዓመታዊ-ክብረ በዓል (ህዳር) 2025
  • መስቀል – ፳፻፲፰ ዓ.ም.
  • መስቀል – ፳፻፲፰ ዓ.ም. — ፎቶ
  • አዲስ አመት – ፳፻፲፰ ዓ.ም.

በፌስቡክ ያግኙን

© ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትሮንዳሔም, St. George EOTC Trondheim , በአጥቢያ ዶት ኮም የተሰራ
ኢሜይል | አጥቢያ ፖርታል
Link to: ልዩ መንፈሳዊ የሕፃናት ቀን በአጥቢያችን በታላቅ ድምቀት ተከበረ Link to: ልዩ መንፈሳዊ የሕፃናት ቀን በአጥቢያችን በታላቅ ድምቀት ተከበረ ልዩ መንፈሳዊ የሕፃናት ቀን በአጥቢያችን በታላቅ... Link to: የ ፳፻፱ ዓ.ም መስቀል ደመራ በዓል በድምቀት ተከበረ፤ የ፫ ቀናት መንፈሳዊ ጉባዔም ተካሄደ Link to: የ ፳፻፱ ዓ.ም መስቀል ደመራ በዓል በድምቀት ተከበረ፤ የ፫ ቀናት መንፈሳዊ ጉባዔም ተካሄደ የ ፳፻፱ ዓ.ም መስቀል ደመራ በዓል በድምቀት ተከበረ፤...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top