በኖርዌይ ትሮንድሃይም ምስራቀ ፀሀይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አመታዊ የሰማእቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ክብረ በዓልን እና የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የስደቷን መታሰቢያ በዓል በደማቅ ሁኔታ ተከበረ
“ይፈትኑት ዘንድ ነው እንጂ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው መከራ አያገኘውም ከመከራዪቱም ይድናል።” መጽሀፈ ሲራክ ምዕ፡ 36 ፥ 1
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በኖርዌይ ትሮንድሃይም ምስራቀ ፀሀይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አመታዊ የሰማእቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ክብረ በዓልን እና የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የስደቷን መታሰቢያ (ፅጌ ማህሌት) መምህር በመጋበዝ ህዳር 5 አና 6 2019 ዓ፡ም
ከእኩለ ሌሊት ጀምሮ በማህሌት፣ በወረብ፣ በኪዳን፣ በቅዳሴ፣ በህፃናት መዝሙር፣ በትምህርት የተሞላ በጣም ብዙ ምእመናን በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከብሯል።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።