በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንየትሮንዳሔም ምሥራቀ ፀሐይ ቅ/ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ እኛ
  • የፎቶ ማኅደሮች
  • ያግኙን
  • Menu Menu

የ፳፻፱ የጌታችን ስቅለት እና ትንሣኤ በዓላት በቤተክርስቲያናችን በደማቁ ተከበረ

ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን

ሞተ ወኬዶ ለሞት

ለእለ ውስተ መቃብር

ወሃበ ሕይወተ ዘለዓለመ ዕረፍተ።

የ፳፻፱ ዓ.ም የጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት እና ትንሣኤ በዓላት በቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በትሮንዳሔም በድምቀት ተከበረ። በዓላቱ ከስዊድን ተጋብዘው በመጡት አባታችን መልአከ ህይወት ፍስሐ አባ ገብረማርያም ቢምረው እና በርካታ ቁጥር ባለው የትሮንዳሄምና አካባቢው ምእመን ሱታፌ በተለያዩ አገልግሎቶች ተከብሯል።

ዕለተ ዓርብ ሚያዝያ ፮፥፳፻፱ ዓ.ም በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን መሠረት የጌታችንን ስቅለት በሚያወሱ ምንባባት፣ ሕማሙን በሚዘክሩ ጸሎቶች እንዲሁም በስግደት ያለፈ ሲሆን፤ በመጨረሻም ዕለቱን የተመለከተ ትምህርት ተሰጥቶ በቡራኬ የዕለቱ መርሃ ግብር ተፈጽሟል።

ቅዳሜ ምሽት ከ20:00 ሰዓት ጀምሮ የጌታችንን ትንሣኤ የሚያወድስ ሥርዓት ከምንባባትና ወረቦች ጋር ከተከናወነ በኋላ በሥርዓተ ቅዳሴና ቡራኬ መርሐ ግብሩ ተፈጽሟል። በዓሉን ለመካፈል የተገኘውም ህዝበ ክርስቲያን ለበዓሉ የተዘጋጀውን ጸበል ጸዲቅ ቀምሰው ወደየቤታቸው በሰላም ተመልሰዋል።

የበዓሉን አከባበር በፎት ይመልከቱ!

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotc-trondheim.no/a/wp-content/uploads/logo-trondheim.svg 0 0 tc https://eotc-trondheim.no/a/wp-content/uploads/logo-trondheim.svg tc2017-04-21 09:30:372018-10-11 14:45:17የ፳፻፱ የጌታችን ስቅለት እና ትንሣኤ በዓላት በቤተክርስቲያናችን በደማቁ ተከበረ
Search Search

በቅርብ ግዜ የተለቀቁ

  • የሊቀ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ የቅዳሴ ቤቱ ዓመታዊ ክብረ በዓል ህዳር ፮ እና ፯፥ ፳፻፲፰ ዓ.ም በድምቀት ተከበረ
  • ሊቀ-ሰማዕቱ-ቅዱስ-ጊዮርጊስ-ዓመታዊ-ክብረ በዓል (ህዳር) 2025
  • መስቀል – ፳፻፲፰ ዓ.ም.
  • መስቀል – ፳፻፲፰ ዓ.ም. — ፎቶ
  • አዲስ አመት – ፳፻፲፰ ዓ.ም.

በፌስቡክ ያግኙን

© ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትሮንዳሔም, St. George EOTC Trondheim , በአጥቢያ ዶት ኮም የተሰራ
ኢሜይል | አጥቢያ ፖርታል
Link to: የደብረ ዘይት በዓል በድምቀት ተከበረ Link to: የደብረ ዘይት በዓል በድምቀት ተከበረ የደብረ ዘይት በዓል በድምቀት ተከበረ Link to: የ፳፻፱ ዓ.ም. የስቅለት እና ትንሣኤ በዓላት አከባበር Link to: የ፳፻፱ ዓ.ም. የስቅለት እና ትንሣኤ በዓላት አከባበር የ፳፻፱ ዓ.ም. የስቅለት እና ትንሣኤ በዓላት አ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top