በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንየትሮንዳሔም ምሥራቀ ፀሐይ ቅ/ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ እኛ
  • የፎቶ ማኅደሮች
  • ያግኙን
  • Menu Menu

በቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትሮንዳሔም የደብረ ዘይት በዓል በድምቀት ተከበረ

በቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትሮንዳሔም መጋቢት ፳፬ ቀን ፳፻፰ ዓም የደብረ ዘይት በዓልን በቅዳሴ፣ በስብከተ ወንጌል እና በያሬዳዊ ዝማሬ ከስቶክሆልም ስዊድን የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ ብርሃን አባ ገብረ ጊዮርጊስ ካሣዬን በመጋበዝ፤ በትሮንዳሄምና አካባቢው የሚገኙ ኦርቶዶክሳዊያን ምዕመናን በተገኙበት በዓሉ በድምቀት ተከብሯል።

በዓሉ በመካከለኛው አውሮፓ የስዓት አቆጣጠር ከንጋቱ 06:00 ሰዓት በጸሎት ተጀምሮ በዓሉን የሚያወሱ ከቅዱሳት መጽሃፍት በመነበብ የኪዳንና የቅዳሴ መርሃ ግብር ተካሂዷል። ከሥርዓተ ቅዳሴው በኋላ እለቱን የተመለከቱ የንስሃ መዝሙራት በአጥቢያው መዘምራን ቀርቧል። በመቀጠልም የደብረ ዘይት በዓልን በተመለከተ ሰፋ ያለ ትምህርት በመልአከ ብርሃን አባ ገብረ ጊዮርጊስ ቀረቦ የእለቱ መርሐ ግብር በአባታችን የማሳረጊያ ጸሎት ተፈጽሟል።

በመጨረሻም በመርሃ ግብሩ የተሳተፈው ምእመናን ወ ምእመናት ለበዓሉ የተዘጋጀውን ጸበል ጸዲቅ ለበረከት እየቀመሰ በሰላም ወደ ቤቱ ተሸኝቷል።

የበዓሉን አከባበር በፎቶ ይመልከቱ!

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotc-trondheim.no/a/wp-content/uploads/logo-trondheim.svg 0 0 tc https://eotc-trondheim.no/a/wp-content/uploads/logo-trondheim.svg tc2016-04-08 15:52:012018-10-11 14:45:16በቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትሮንዳሔም የደብረ ዘይት በዓል በድምቀት ተከበረ
Search Search

በቅርብ ግዜ የተለቀቁ

  • የሊቀ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ የቅዳሴ ቤቱ ዓመታዊ ክብረ በዓል ህዳር ፮ እና ፯፥ ፳፻፲፰ ዓ.ም በድምቀት ተከበረ
  • ሊቀ-ሰማዕቱ-ቅዱስ-ጊዮርጊስ-ዓመታዊ-ክብረ በዓል (ህዳር) 2025
  • መስቀል – ፳፻፲፰ ዓ.ም.
  • መስቀል – ፳፻፲፰ ዓ.ም. — ፎቶ
  • አዲስ አመት – ፳፻፲፰ ዓ.ም.

በፌስቡክ ያግኙን

© ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትሮንዳሔም, St. George EOTC Trondheim , በአጥቢያ ዶት ኮም የተሰራ
ኢሜይል | አጥቢያ ፖርታል
Link to: የሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ የንግስ ክብረ በዓል Link to: የሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ የንግስ ክብረ በዓል የሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ የንግስ... Link to: በቅዱስ ጊዮርጊስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በትሮንዳሔም የሆሳዕና በዓል በድምቀት ተከበረ። Link to: በቅዱስ ጊዮርጊስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በትሮንዳሔም የሆሳዕና በዓል በድምቀት ተከበረ። በቅዱስ ጊዮርጊስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በትሮንዳሔም የሆሳዕና...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top