ሰባቱ ምስጢራተ-ቤተክርስቲያን ለሦስት ተከታታይ ሳምንታት በትሮንዳሔም ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰ/ት/ቤት ተሰጠ

በኖርዎዌይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የትሮንዳሔም ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰንበት ትምህርት ቤት ለሦስት ተከታታይ ሳምንታት ማለትም ጥቅምት ፲፯ እና ፳፬ እንዲሁም ህዳር ፩ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ስለ ሰባቱ ምስጢራተ-ቤተክርስቲያን ተከታታይ ትምህርት ለአባላት በዕለተ ሰንበት ከጸሎት በኋላ ተሰጥቷል። ተከታታይ ትምህርቱ የተዘጋጀው የሰንበት ትምህርት ቤቱ አባላት ስለ ቅዱስ ቁርባንና ቅዱስ ጋብቻ ትምህርት እንዲሰጣቸዉ በጠየቁት መሰረት ነው። ትምህርቱን የሰጠዉ ዲ/ን አብይ ከኦታ ሲሆን በትምህርቱ ወቅት አባላቱ ላቀረቡት የተለያዩ ጥያቄዎች መልሶችና ማብራሪያዎች ተሰጥተዋል።

መርሃግብሩን በፎቶ ይመልከቱ