በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንየትሮንዳሔም ምሥራቀ ፀሐይ ቅ/ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ እኛ
  • የፎቶ ማኅደሮች
  • ያግኙን
  • Menu Menu

የጥምቀት በዓል በኖርዌይ በድምቀት ተከበረ

በኖርዌይ በተለያዩ ከተማ የሚገኙት ስድስት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናት ማለትም የኦስሎ ቅዱስ ገብርኤል፤ የስታቫንጋር መድኃኔዓለም፤ የክርስቲያንሳንድ ቅድስት ድንግል ማርያም፤ የበርገን እመቤታችንና ቅዱስ ሚካኤል እና የትሮንዳሔም ቅዱስ ጊዮርጊስ ታቦታት አንድ ላይ በመሆን የጌታችን የአምላካችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን በዓለ ጥምቀት በበርገንበታላቅ ድምቀት አከበሩ። በዓሉ በኖርዌይና ከተለያዩ ሃገራት በመጡ አባቶች ካህናትና ምእመናን በተገኙበት በቤተ ክርስቲያናችን ስርዓት መሰረት ከከተራ ጀምሮ ማለትም ጥር ፲ እና ፲፩ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም በደማቅ መንፈሳዊ አገልግሎት ተከበረ። የጥምቀት በዓል በኖርዌይ በአንድነት መከበር የጀመረው በ፳፻፬ ዓ.ም በኦስሎ ከተማ ሲሆን እንደዚህ ቁጥራቸው በዛ ባሉ ታቦታት ሲከበር ግን የመጀመሪያ ነው። ይህ በዓል ባለፈው ዓመትም በስታቫንገር እንደዚሁ በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ እንደነበር ይታወሳል።

በመጨረሻም የበርገን እመቤታችንና ቅዱስ ሚካኤል ታቦታት በክብር ወደ መንበራቸው ከገቡ በኋላ ከተለያዩ ከተማ በክብር ከየአብያተ ክርስቲያናቱ ወጥተው ወደ በርገን ከተማ ለጥምቀተ በዓል የሄዱት ታቦታት በአባቶች ወደ የመጡበት በክብር ተመልሰዋል፡፡

በቀጣይም ይህን የአንድነት የጥምቀት በዓል አከባበር ተራው ያልደረሳቸው አጥቢያዎች በኃላፊነት ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የበዓሉን አከባበር በፎቶ ይመልከቱ

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotc-trondheim.no/a/wp-content/uploads/logo-trondheim.svg 0 0 tc https://eotc-trondheim.no/a/wp-content/uploads/logo-trondheim.svg tc2014-01-22 19:58:452018-10-11 14:45:15የጥምቀት በዓል በኖርዌይ በድምቀት ተከበረ
Search Search

በቅርብ ግዜ የተለቀቁ

  • የሊቀ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ የቅዳሴ ቤቱ ዓመታዊ ክብረ በዓል ህዳር ፮ እና ፯፥ ፳፻፲፰ ዓ.ም በድምቀት ተከበረ
  • ሊቀ-ሰማዕቱ-ቅዱስ-ጊዮርጊስ-ዓመታዊ-ክብረ በዓል (ህዳር) 2025
  • መስቀል – ፳፻፲፰ ዓ.ም.
  • መስቀል – ፳፻፲፰ ዓ.ም. — ፎቶ
  • አዲስ አመት – ፳፻፲፰ ዓ.ም.

በፌስቡክ ያግኙን

© ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትሮንዳሔም, St. George EOTC Trondheim , በአጥቢያ ዶት ኮም የተሰራ
ኢሜይል | አጥቢያ ፖርታል
Link to: በትሮንዳሔም የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ተቋቋመ Link to: በትሮንዳሔም የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ተቋቋመ በትሮንዳሔም የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን... Link to: የትሮንዳሔም ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላላ ጉባኤውን አደረገ Link to: የትሮንዳሔም ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላላ ጉባኤውን አደረገ የትሮንዳሔም ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላላ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top