የ፳፻፮ ዓ.ም. የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ ክብረ በዓል በደመቀ መልኩ ተከበረ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የትሮንዳሔም ቅዱስ ጊዮርጊስ ደብር የ፳፻፮ ዓ.ም. የዳግም ትንሣኤንና የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ ክብረ በዓላት ከተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት ተጋብዘው በመጡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ የሰንበት ት/ቤት መዘምራን፣ ምእመናን እና ምእመናት በተገኙበት ዓርብ ሚያዚያ ፲፯ እና ቅዳሜ ሚያዚያ ፲፰ በታላቅ ድምቀት አከበረ። በዓሉ በማሕሌት፣ በቅዳሴ፣ በትምህርተ ወንጌልና በመዝሙር የተከበረ ሲሆን ያሬዳዊ ዝማሬም በደብሩ መዘምራን ቀርቧል። በተጨማሪም የላቫንጋርና ቅዱስ ሚካኤል የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መዘምራን ያሬዳዊ ዝማሬን አቅርበዋል።
በዓሉ ላይ በመገኘት በስራ፣ በጸበል ጸዲቅና በተለያዩ መንገዶች ተሳትፎ በማድረግ ለዝግጅቱ መሳካት ብሎም ለበዓሉ ድምቀት ላደረጋችሁልን ተሳትፎ ሁሉ በሊቀ ሰማዕቱ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም ምስጋናችንን እናቀርባለን።