በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንየትሮንዳሔም ምሥራቀ ፀሐይ ቅ/ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ እኛ
  • የፎቶ ማኅደሮች
  • ያግኙን
  • Menu Menu

የጌታችን ስቅለት እና ትንሣኤ በዓላት በልዩ ልዩ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች በደማቅ ሁኔታ ተከበረ

&nbsp

ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን

ሞተ ወኬዶ ለሞት

ለእለ ውስተ መቃብር

ወሀበ ሕይወተ ዘለዓለመ ዕረፍተ።

&nbsp

&nbsp

የ፳፻፰ ዓ.ም የጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት እና ትንሣኤ በዓላት በቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትሮንዳሔም በድምቀት ተከበረ። በዓላቱ በአባታችን አባ ገብረ ማርያም ቢምረው እና መጋቤ ሐዲስ ምሥጢረሥላሴ ማንአየ መሪነት እና በርካታ ቁጥር ባለው ምእመን ሱታፌ በተለያዩ አገልግሎቶች ተከብረዋል።

ዕለተ አርብ ሚያዝያ ፳፩፥፳፻፰ ዓ.ም በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን መሠረት የጌታችንን ስቅለት በሚያወሱ ምንባባት፣ ሕማሙን በሚዘክሩ ጸሎቶች እንዲሁም በስግደት ያለፈ ሲሆን፤ “አምላክ ዓለምን ከፈጠረበት ይልቅ ሰው ሆኖ ዓለሙን ያዳነበት ጥበብ ይበልጣል” እንደተባለ የጌታችንን ረቂቅ የማዳን ሥራ እና ነገረ-መስቀሉን በተመለከተ በመጋቤ ሐዲስ ምሥጢረሥላሴ ትምህርት ተሰጥቷል።

ቅዳሜ ማለዳ ለቀዳም ስዑር እለት የሚደረጉት ጸሎትና ምንባባት ከተከናወኑ በኋላ ቀኑን የተመለከተ አጠር ያለ ትምህርት በመጋቤ ሐዲስ ምሥጢረሥላሴ ተሰጥቶ የማለዳው መርሐ ግብር ፍጻሜ ሆኗል።

ቅዳሜ ምሽት ከ 22:00 ሰዓት ጀምሮ የጌታችንን ትንሳዔ የሚያወድስ ሥርዓት ከምንባባትና ወረቦች ጋር ከተከናወነ በኋላ በኪዳንና በሥርዓተ ቅዳሴ የመርሐ ግብሩ ፍጻሜ ሆኗል። በዓሉን ለመካፈል የተገኘውም ህዝበ ክርስቲያንም ለበዓሉ የተዘጋጀውን የጾም መፈሰኪያ ጸበል ጸዲቅ እየቀመሰ ወደየቤቱ በሰላም ተመልሷል።

የበዓሉን አከባበር በፎቶ ይመልከቱ!

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotc-trondheim.no/a/wp-content/uploads/logo-trondheim.svg 0 0 tc https://eotc-trondheim.no/a/wp-content/uploads/logo-trondheim.svg tc2016-05-04 22:10:152018-10-11 14:45:16የጌታችን ስቅለት እና ትንሣኤ በዓላት በልዩ ልዩ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች በደማቅ ሁኔታ ተከበረ
Search Search

በቅርብ ግዜ የተለቀቁ

  • የሊቀ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ የቅዳሴ ቤቱ ዓመታዊ ክብረ በዓል ህዳር ፮ እና ፯፥ ፳፻፲፰ ዓ.ም በድምቀት ተከበረ
  • ሊቀ-ሰማዕቱ-ቅዱስ-ጊዮርጊስ-ዓመታዊ-ክብረ በዓል (ህዳር) 2025
  • መስቀል – ፳፻፲፰ ዓ.ም.
  • መስቀል – ፳፻፲፰ ዓ.ም. — ፎቶ
  • አዲስ አመት – ፳፻፲፰ ዓ.ም.

በፌስቡክ ያግኙን

© ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትሮንዳሔም, St. George EOTC Trondheim , በአጥቢያ ዶት ኮም የተሰራ
ኢሜይል | አጥቢያ ፖርታል
Link to: በቅዱስ ጊዮርጊስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በትሮንዳሔም የሆሳዕና በዓል በድምቀት ተከበረ። Link to: በቅዱስ ጊዮርጊስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በትሮንዳሔም የሆሳዕና በዓል በድምቀት ተከበረ። በቅዱስ ጊዮርጊስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በትሮንዳሔም የሆሳዕና... Link to: የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል ተከበረ Link to: የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል ተከበረ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top