የመስቀል በዓል አከባበር
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ! በትሮንዳሔም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ የቅዱስ ጊዮርጊስ ሰ/ት/ቤት የደመራ በዓልን ሐሙስ መስከረም ፲፮ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ደመራ በማብራት እና በዝማሬ በድምቀት አከበረ። የመስቀልን በዓል ምክንያት በማድረግም በዓመታዊው መርሃ ግብራችን መሰረት ቅዳሜ መስከረም ፲፰ ቀን ፳፻፮ዓ.ም. በአካባቢው የሚኖሩ ምእመናንና ምዕመናት በተገኙበት የቅዳሴ መርሃ ግብር ተደርጓል። ዘመነ ማርቆስ የሰላም፣ የፍቅር፣ የጤና፣ የንስሐና የአገልግሎት ዘመን እንዲሆን የእግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃድ ይሁንልን። የሥላሴ ቸርነት፣ የእመቤታችን አማላጅነት፣ የመስቀሉ በረከት ይደርብን፡፡ አሜን።