በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንየትሮንዳሔም ምሥራቀ ፀሐይ ቅ/ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ እኛ
  • የፎቶ ማኅደሮች
  • ያግኙን
  • Menu Menu

ለ፪ ቀናት የቆየ ልዩ መንፈሳዊ ጉባዔ ተካሄደ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሰሜን ምዕራብ አውሮጳ ሃገረ ስብከት የትሮንዳሔም ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ለአገልግሎት ከኢትዮጵያ ወደ አውሮጳ በመጡት በኩረ መዘምራን ኪነጥበብ ወ/ቂርቆስ እና መጋቤ ሐዲስ ምሥጢረ ሥላሴ ማናዬ ለ፪ ቀናት የቆየ የዝማሬና የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ተካሄደ። ጉባዔው ከትሮንዳሔምና አካባቢው በተገኙ ምዕመናን ቅዳሜ መስከረም ፳፰ በ 9:00 ሰዓት እንዲሁም መስከረም ፳፱ በ 10:30 ሰዓት ስለሃገራችን ሰላምና መረጋጋት የዘወትርና የምኅላ ጸሎት በማድረስ ተጀምሯል። በመቀጠልም ያሬዳዊ መዝሙሮች በበኩረ መዘምራን ኪነጥበብ ከስብከተ ወንጌል አገልግሎት በፊትና በኋላ ተዘምረዋል። የሁለቱም ቀናት የስብከተ ወንጌል አገልግሎት የተሰጠው በመጋቤ ሐዲስ ምሥጢረ ሥላሴ ነበር። በተጨማሪም ስለ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙር ከምዕመናን የቀረቡ የተለያዩ ጥያቄዎች በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል። ከመርሃግብራቱ ፍጻሜም በኋላ ምዕመናን የተዘጋጀውን ዝክር ቀምሰው ወደየመጡበት በሰላም ተሸኝተዋል።

ጉባዔውን በምስል ይመልከቱ!

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotc-trondheim.no/a/wp-content/uploads/logo-trondheim.svg 0 0 tc https://eotc-trondheim.no/a/wp-content/uploads/logo-trondheim.svg tc2016-10-14 20:00:222018-10-11 14:45:17ለ፪ ቀናት የቆየ ልዩ መንፈሳዊ ጉባዔ ተካሄደ
Search Search

በቅርብ ግዜ የተለቀቁ

  • የሊቀ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ የቅዳሴ ቤቱ ዓመታዊ ክብረ በዓል ህዳር ፮ እና ፯፥ ፳፻፲፰ ዓ.ም በድምቀት ተከበረ
  • ሊቀ-ሰማዕቱ-ቅዱስ-ጊዮርጊስ-ዓመታዊ-ክብረ በዓል (ህዳር) 2025
  • መስቀል – ፳፻፲፰ ዓ.ም.
  • መስቀል – ፳፻፲፰ ዓ.ም. — ፎቶ
  • አዲስ አመት – ፳፻፲፰ ዓ.ም.

በፌስቡክ ያግኙን

© ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትሮንዳሔም, St. George EOTC Trondheim , በአጥቢያ ዶት ኮም የተሰራ
ኢሜይል | አጥቢያ ፖርታል
Link to: የ ፳፻፱ ዓ.ም መስቀል ደመራ በዓል በድምቀት ተከበረ፤ የ፫ ቀናት መንፈሳዊ ጉባዔም ተካሄደ Link to: የ ፳፻፱ ዓ.ም መስቀል ደመራ በዓል በድምቀት ተከበረ፤ የ፫ ቀናት መንፈሳዊ ጉባዔም ተካሄደ የ ፳፻፱ ዓ.ም መስቀል ደመራ በዓል በድምቀት ተከበረ፤... Link to: የጥምቀት በዓል ለመጀመሪያ ጊዜ በትሮንዳሔም በድምቀት ተከበረ Link to: የጥምቀት በዓል ለመጀመሪያ ጊዜ በትሮንዳሔም በድምቀት ተከበረ የጥምቀት በዓል ለመጀመሪያ ጊዜ በትሮንዳሔም በድምቀት...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top